በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ፓርላማ


ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ ሱድን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር
ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ ሱድን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር

ደቡብ ሱዳን ውስጥ የሀገሪቱን ፓርላማ አፍርሶ፣ በአዲስ መልክ ለማስተካከል ተይዞ ነበረው የጊዜ ገደብ፣ ባለፈው እሁድ ማለፉ ታወቀ።

የደቡብ ሱድን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር፣ የወቅቱን ቢሄራዊ ሸንጎ፣ እስከ እሁድ በነበረው ጊዜ እንዲያፈርሱ፣ የሀገሪቱን የሰላም ሥምምነት የሸመገለው የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች የልማት ትብብር ባለሥልጣን፣ ጥሪ አድርጎ ነበር።

ከአምስት ወራት በፊት፣ ከፊል የውህደት መንግሥት ተመስርቶ ነበር። ነገር ግን ምክርቤቱ በአዲስ መልክ መስተካከል ነበረበት። ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የክፍላተ-ግዛት አስተዳዳሪዎችን የሾሙት፣ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ነው ተብሏል።

የደቡብ ሱዳን የማስታወቅያ ሚኒስትር ሚካኤል ማኩይ፣ ምክር ቤቱን የማስተካከሉ ተግባር ገና እየተሰራበት ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG