በደቡብ ሱዳን በጎርፍ በድርቅና በግጭት የተነሳ መጪው ሃምሌ ላይ ሲደረስ ከሰባት ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ ለምግብ ቀውስ ይጋለጣል ተብሏል።
ካለፈው የአውሮፓ 2021 ጀምሮ የምግብ ዋስትና ቀውሱ እየተባባሰ መሆኑ ነው የተገለጸው።
የታጣቂ ኃይሎች ግጭት መበራከቱ፣ የህዝብ መፈናቀል፣ ድርቅና ጎርፍ የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ለችግሩ አስተዋጽኦ ማደረጋቸውን ነው የ ተመድ እና የደቡብ ሱዳን መንግሥት በጋራ ያወጡት ሪፖርት ያመለከተው።
በጆንጊሌ እና በፒቦር እንዲሁም ዩኒቲ እና ሌክስ ክፍላተ ሀገር እስከ መጪው የሃምሌ ወር ሰማኒያ ሰባት ሺህ ህዝብ እጅግ በበረታ ቸነፈር ይጠቃሉ ብሏል ሪፖርቱ።