በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ምርጫ በሚቀጥለው ዓመት እንደሚካሄድ ተገለጸ


የደቡብ ሱዳን መሪ ሳልቫ ኪር
የደቡብ ሱዳን መሪ ሳልቫ ኪር

· ሳልቫ ኪር እንደሚወዳደሩ አስታወቁ

የደቡብ ሱዳን መሪ ሳልቫ ኪር፤ ሲተላለፍ ቆይቶ፣ ለሚቀጥለው ዓመት ፕሮግራም የተያዘለት ምርጫ፣ በታቀደለት መሠረት እንደሚካሄድና እሳቸውም ለፕሬዚዳትነት እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል፡፡

ኪር ትግሉን በመምራት አገራቸው ከሱዳን ነጻነቷን እንድትቀዳጅ ካበቁበት እ.አ.አ ከ2011 ጀምሮ የአገሪቱ ብቸኛው ፕሬዚዳንት ሆነው ቆይተዋል፡፡

በዓለም ወጣቷ አገር፣ በኪር የሥልጣን ዘመን በርካታ ቀውሶችን ስታስተናግድ ቆይታለች፡፡

በኪር እና በምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ደካማ ግኑኝነት ላይ በተመሰረተ መንግሥትም የምትተዳደር መሆኗ ተመልክቷል፡፡

እስከ አሁን ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደር ያስታወቀ እጩ ባይኖርም ታሪካዊ ባላንጣቸው ማቻር ይወዳደራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

XS
SM
MD
LG