በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን ላይ የመሣሪያ እገዳ እንደቀጥል ተጠየቀ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ደቡብ ሱዳን ላይ ጥሎት የነበረውን የጦር መሣሪያ ዕገዳ እንዲያድስ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ቡድን ትናንት ባወጣው መግለጫ ደቡብ ሱዳን ውስጥ “ተኩስ የማቆም ስምምነት ቢደረስም፤ ባለፈው የካቲት የአንድነት መንግሥት ቢመሠረትም በሲቪሎች ላይ የሚፈፀሙት ግፍ፣ የጭካኔ አድራጎቶችና የጦር ወንጀሎች በዚህ የአውሮፓ ዓመት በአራት እጥፍ ማሻቀቡን” አመልክቷል።

የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ በደቡብ ሱዳን ላይ የመሣሪያ ዕገዳ የጣለው /እአአ/ በግንቦት 2011 ዓ.ም. ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት በተከታታይ አራዝሞታል።

ዋና መሥሪያ ቤቱ ኒው ዮርክ የሚገኘው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዕገዳው እንዲራዘም የጠየቀው “የመንግሥቱ ኃይሎች የያዟቸውን የጦር መሣሪያዎች የሚጠቀሙባቸው ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በመሆኑና ብዙ ጊዜም የጭካኔና የግፍ አድራጎቶቹን የሚፈፅሙት እራሣቸው በመሆናቸው ነው” ብለዋል የቡድኑ ከፍተኛ አማካሪና የመሣሪያ ጉዳዮች መርማሪ ብራያን ካስትነር ትናንት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል።

ደቡብ ሱዳን ላይ ተጥሎ በቆየው የጦር መሣሪያ ዕገዳ አፈፃፀምና በውጤቱ ላይ የፀጥታ ምክር ቤቱ ከታኅሣስ 6 በፊት የመንፈቅ ግምገማ ከማድረጉ በፊት ነው አምነስቲ ሪፖርቱንና የማራዘሚያ ጥያቄውን ያቀረበው።

በማዕከላዊ ኢኳቶሪያ ክልል የበዙ ከህግ አግባብ ውጭ የሆኑ ግድያዎችን፣ በኃይል የማፈናቀል እንቅስቃሴዎችን፣ የመድፈር፣ የማሰቃየት አድራጎቶችንና የሲቪሎችን ንብረት ማውደም አድራጎቶችን አምነስቲ መመዝገቡንና በተለይ ካለፈው ሚያዝያ እስከ ሰኔ የነበሩት ወራት እጅግ የከፉ እንደነበሩ ካስትነር ገልፀው እነዚህ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በሃገሪቱ ላይ ተጥሎ የቆየው የመሣሪያ እገዳ እንዲቀጥል የሚያስገድዱ መሆናቸውን አጠንክረው አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG