በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ኮሪያ ምርጫ እና "ያልተወደዱት እጩዎቿ"


የፕሬዚዳንታዊ እጩዎች ፖስተሮች በምርጫ ጣቢያዎች፤ በዋና ከተማ ሲኦል፣ ደቡብ ኮሪያ
የፕሬዚዳንታዊ እጩዎች ፖስተሮች በምርጫ ጣቢያዎች፤ በዋና ከተማ ሲኦል፣ ደቡብ ኮሪያ

ደቡብ ኮሪያውያን ከነገ በስቲያ ረቡዕ አዲሱን ፕሬዚዳንታቸውን ለሚመርጡበት ምርጫ የተካሄደው ከፍተኛ የሙስና ውንጀላ እና መረር ያለ የእርስ በእርስ ስም መጠፋፋት የተስተዋለበት የምረጡኝ ዘመቻ ተጠናቀቀ።

ደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የወጣቶች ሥራ አጥነት፣ ጣሪያ የነካውን የቤት ዋጋ፣ እና የኮሮናቫይረስ በወረርሽ ያስከተከለውን የምጣኔ ኃብት መዳከም ጨምሮ አስቸኳይ ትኩረት የሚሹ ችግሮች እጥረት የለባትም ነው የተባለው።

ይሁንና ለመራጩ ሕዝብ አንገብጋቢ ናቸው በተባሉት ጉዳዮች ዙሪያ የነበሩት ክርክሮች በሁለቱ እጩዎች መካከል በታዩት እና አንዱ ሌላውን ባጠለሹባቸው ታዛቢዎች ከዚህ በፊት ታይተው እና ተሰምተው የማያውቁ ባሏቸው የበረቱ የእርስ በእርስ ውንጀላዎች ተውጠዋል።

የቅድመ ምርጫ ትንበያዎች እንዳሳዩት ከዲሞክራሲ አራማጆች ወገን እጩ ሆነው የቀረቡት፣ የቀድሞው አገረ ገዥ ሊ ዤ - ሙያንግ እና ከወግ አጥባቂው ወገን የሆኑት ተቀናቃኛቸው የቀድሞ አቃቤ ሕግ ዩን ሱክ-ዩል፣ ከፍተኛ ትንቅንቅ በታየበት ምርጫ ተፎካካሪዎቻቸውን በምመራት ላይ ናቸው።

የፖለቲካ ተንታኝ እና ደራሲዋ ኪም ሚንሃ እንዳሉት ካሁን ቀደም ከተለመደው እና እጩዎች በነገሮች ላይ ባሏቸው የአመለካከት አለያም የአላማ ልዩነቶች ላይ ይደረጉ ከነበሩ ፍልሚያዎች ይልቅ ያሁኖቹ በግለሰቡ ላይ የተነጣጠሩ የማጥቂያ ስልቶች የበረከቱበት ነበር። በዚህም የተነሳ “በአገሪቱ የምርጫ ዘመቻዎች ታሪክ ከመቼውም የከፋ ዘመቻ” ተብሏል።

ሁለቱም እጩዎች በእጅጉ የማይወደዱ መሆናቸውን ያመላከቱ የመራጭ አስተያየት ግምገዎችን መሰረት ያደረጉ በርካታ የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ምርጫውን “የማይወደዱ ዕጩዎች ምርጫ” ብለውታል።

ይሁንና ከዋናው የምርጫ ቀን አስቀድሞ በሚደረጉ ምርጫዎች በድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የታዩት ድምጻቸውን ለመስጠት የወጡ ሰዎች ለሰዓታት ተራቸውን ሲጠባበቁ የታዩባቸው ረጃጅም ሰልፎች ሁኔታው በመራጮች ተሳትፎ ላይ ተጽዕኖ ያለማድረጉን አመላክተዋል።

"በዚህ ምርጫ በመራጮች ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው አስተሳሰብ ሌላኛው እጩ እንዳያሸንፍ ለማድረግ ወጥቶ ድምጽ መስጠት የሚል ነው" ሲሉ “ዲሞክራሲ ሰዎች እርስ በእርስ ባለመዋደዳቸው ድምፅ የሚሰጡበት” የተባለው መጽሃፍ ደራሲ እና ተንታኝዋ ኪም አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG