በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ራሳቸውን አገለሉ


ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሴሪል ራማፎሳ
ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሴሪል ራማፎሳ

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሴሪል ራማፎሳ በአንድ የእራት ዝግጅት ላይ አብሯቸው የነበረ እንግዳ በኮሮናቫይረስ የተያዘ መሆኑ ከተሰማ በኋላ ራሳቸውን አግልለው እንደሚገኙ ተገለጸ።

ባለፈው ሳምንት ጆሃንስበርግ ውስጥ ለትምህርት ቤት ገቢ ማሰባሰቢያ ድግስ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንቱ በእራቱ ላይ ከነበሩት ሠላሳ አምስት እንግዶች አንደኛው ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ማክሰኞ እለት ከተነገራቸው በኋላ ራሳቸውን ለይተዋል ሲል ቃል አቀባያቸው ገልጿል።

ፕሬዚዳንቱ ምንም የህመም ምልክት የላቸውም ራሳቸውን ለይተው ሥራቸውን እያከናወኑ ናቸው ብሏል።

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ባለፉት ቅርብ ሳምንታት የቫይረሱ ስርጭት አሻቅቧል። በአሁኑ ጊዜ ከ719,714 በላይ ተጋላጮች ያሉ ሲሆን 19,111 ሰዎች ሞተዋል።

XS
SM
MD
LG