በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ "ስፐትኒክ ቪ" የተባለውን የኮቪድ ክትባት ውድቅ አደረገች


ስፐትኒክ ቪ የኮቪድ ክትባት
ስፐትኒክ ቪ የኮቪድ ክትባት

የደቡብ አፍሪካ የመድሃኒት ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤት ስፐትኒክ ቪ ለተባለው በሩስያ የተሰራ የኮቪድ ክትባት ለአጣዳፊ ጥቅም እንዲውል አልፈቅድም አለ፤ ክትባቱ ወንዶችን ለኤችአይቪ የመጋለጣቸውን አደጋ ከፍ ያደርጋል የሚል ሥጋት እንዳለው ነው ያስታወቀው።

የሩስያውን ክትባት የመሳሰሉት በለዘቡ አዴኖ ቫይረስ የሚባሉ ቫይረሶች የተሰሩ መሆናቸውን የሚገልጹ የቀደሙ ጥናቶችን የደቡብ አፍሪካው የመድሃኒት ተቆጣጣሪ ለደረሰበት ውሳኔ በምክንያትነት ጠቅሷል።

የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል /ሲዲሲ/ እነዚህን አዴኖ ቫይረሶች ትኩሳት፣ የሳምባ ምች እና የጉሮሮ ህመም የመሳሰሉት የሚያስከትሉ የተለመዱ ቫይረሶች ብሎ እንደሚገልጻቸው የደቡብ አፍሪካው የመድሃኒት ተቆጣጣሪ ድርጅት ጠቅሷል።

ስፐትኒክ ቪ የኮቪድ ክትባትን የሰራው የሩስያው ጋማላያ ማዕከል ደቡብ አፍሪካ ያሰማችውን ስጋት ሙሉ በሙሉ መሰረተ ቢስ ሲል አጣጥሎታል።

XS
SM
MD
LG