ዋሺንግተን ዲሲ —
ደቡብ አፍሪካ የተቀበለችው የአስትራዝኔካው ክትባት በሀገሪቱ በብዛት በተዛመተው በጣም ተላላፊው በሁነው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ላይ ብዙም ውጤታማ ላይሆን እንደሚችል የሃገሪቱ የጤና ጠቢባን ተናገሩ።
በዚህ ዜና ሳቢያ የሀገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት በአፍሪካ ግዙፉ እንደሚሆን የተገለጸውን የክትባት ዘመቻ እንዳይጀመር ለማድረስ ሳይገደዱ አይቀሩም ተብሏል
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በተካሄደ ጥናት መሰረት ይህ ክትባት 501 ዋይ ወይም ቪ2 ተብሎ በሚታወቀው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ላይ ሙሉ የመከላከል አቅም የሚኖረው አይመስልም።
የዓለም የጤና ድርጅት በዚህ ጉዳይ ዛሬ ስብሰባ አድርጎ እንደሚነጋገር ነው ዘገባው ጨምሮ ያመለከተው።
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እስካሁን ከአርባ ስድስት ሽህ በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ይህ ዜና ድንጋጤ ፈጥሯል።
የደቡብ አፍሪካው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ በሰላሳ ሁለት ሀጋሮች እንደተዛመተ ተገልጿል።