ዋሺንግተን ዲሲ —
ደቡብ ኮሪያ፣ አገሯ ላይ የሚካሄደውን የክረምት ኦሎምፒክ በተመለከተ፣ ከቀንደኛ ጠላቷ ሰሜን ኮሪያ ጋር በከፍተኛ ልዑካን አማካኝነት መወያየት እንደምትሻ አስታወቀች።
የደቡብ ኮሪያ የአንድነት ጉዳይዮች ሚኒስትር ቾ መዮንግ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ሴኡል፣ ከፍተኛ መልዕክተኞቿን፣ የቃል ኪዳን ሰፈር ተብሎ ወደሚታወቀውና ደቡቡንና ሰሜኑን የሚለየው ቀጣና ወደሚገኝበት ጳንሙንጆም በመላክ ከሰሜን ኮሪያ ዲፕሎማቶች ጋር እንዲወያዩ ሁኔታዎችን ታመቻቻለች ብለዋል።
ውይይቱ፣ እኤአ ካለፈው ታህሣሥ 2015 ወዲህ፣ በሴኡል እና በጵዮንግያንግ መካከል በከፍተኛ ደረጃ የሚካሄድ የመጀመሪያው ግንኙነት እንደሚሆንም ታውቋል።
የሰሜኑ መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ በትናንቱ የአዲስ ዓመት መግቢያ ንግግራቸው፣ ፕዮንግያንግ፣ ለክረምቱ ኦሎምፒክ ውድድር፣ ስፖርተኞቿን ወደ ደቡብ ኮሪያ ለመላክ እያሰበችበት መሆኗን አውስተዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ