በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሞሃመድ ባዙም ልጅ “ለግዜው” ከእስር ተለቀዋል


ፎቶ ፋይል፦ ኒያሜይ፣ ኒዤር
ፎቶ ፋይል፦ ኒያሜይ፣ ኒዤር

ባለፈው ሐምሌ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱት የኒዤር ፕሬዝደንት ሞሃመድ ባዙም ልጅ ትናንት ሰኞ “ለግዜው” ከእሥር እንደተለቀቁ በኒያሜይ የሚገኝ ወታደራዊ ችሎት አስታውቋል።

የኤ.ኤፍ.ፒ ዜና ወኪል ተመልክቼዋለሁ ያለውን የችሎቱን ሰነድ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ከወላጆቻቸው ጋር ባለፈው ሐምሌ ተይዘው የነበሩት ሳሌም ባዙም “ለግዜው” እንዲለቀቁ ተወስኗል።

ወደፊት በተፈለጉ ግዜም ወዲያውኑ ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው ሰነዱ አመልክቷል።

የሳሌም ወላጆች አሁንም በፕሬዝደንታዊ መኖሪያ ቤታቸው እንደታገቱ ናቸው።

ለሞሃመድ ባዙም ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለኤ.ኤፍ.ፒ ዜና ወኪል እንዳስታወቁት፣ የ22 ዓመቱ ሳሌም ባዙም ትናንት ማምሻውን የቶጎ መዲና ወደሆነችው ሎሜ አቅንተዋል።

ሳሌም የተለቀቁት በቶጎ እና ሴራ ሊዮን መንግስታት አሸማጋይነት እንደሆነ ከቶጎ መንግሥት የወጣው መግለጫ አረጋግጧል።

ኒዤር ካለፈው ሐምሌ ወዲህ ሞሃመድ ባዙምን ከሥልጣን ባስወገደው ወታደራዊ ሁንታ በመተዳደር ላይ ስትሆን፣ መሪው ጀኔራል አብዱራህማኔ ቲያኒ አገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመመለስ የሶስት ዓመታት ግዜ እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG