በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮ/ል ጋዳፊ ልጅ በታህሳሱ የሊቢያ ምርጫ ሊወዳደሩ ነው


የቀድሞ የሊቢያ መሪ ኮ/ል ሞአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፊ አል ኢስላም ጋዳፊ
የቀድሞ የሊቢያ መሪ ኮ/ል ሞአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፊ አል ኢስላም ጋዳፊ

የቀድሞ የሊቢያ መሪ ኮ/ል ሞአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፊ አል ኢስላም ጋዳፊ በመጭው ታህሳስ 15 በሚደረገው ምርጫ ለመወዳደር በዕጩነት መመዝገባቸውን አስታወቁ፡፡

ሰይፊ ባለፈው ዕሁድ ሳባኽ ከተማ ለፕሬዚዳንት ዕጩነት ቀርበው የተመዘገቡ ሲሆን፣ በተለይ አባታቸው ኮ/ል ጋዳፊ ጠንካራ ድጋፍ ባላቸው በርካታ ደቡብ ሊቢያ አካባቢዎች እንደሚወዳደሩ ተነግሯል፡፡

በሄግ የሚገኘው የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ቃል አቀባይ ዜናውን ተከትሎ ትናንት እሁድ በሰጡት አስተያየት፣ ከሊቢያን ህዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ፣ ጋዳፊ በሰዓብዊነት ላይ ፈጸመዋል በተባለው ወንጀል ተጠያቂነት ተላልፈው እንዲሰጡ የቀረበው ጥያቄ አሁንም እንዳለና ያልተቀየረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፓሪስ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ካታር አቡዳቢ የሊቢያ ፍርድ ቤት ምን ሊወሰን እንደሚችል ግልጽ አይደለም ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

ባላፈው ዓመት የሊቢያ ፍርድ ቤት በሰይፊ ጋዳፊ ላይ የተፈረደውን የሞት ክስ ውድቅ አድርጎ ከእስር የለቀቃቸው መሆኑን ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG