በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የጊኒ ፕሬዚዳንት ወንድ ልጅና ባለቤታቸው ክስ ተመሰረተባቸው


ዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ክፍለ ሃገር ዳላስ ከተማ የቀድሞ የጊኒ ፕሬዚዳንት ወንድ ልጅና ባለቤታቸው በተንደላቀቀው መኖሪያ ቤታቸው አንዲት ጊኒያዊት ወጣት ለአሥራ ስድስት ዓመታት በባርነት ይዘው አኑረዋል ተብለው በዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ፍ/ቤት ክስ ተመሰረተባቸው።

ዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ክፍለ ሃገር ዳላስ ከተማ የቀድሞ የጊኒ ፕሬዚዳንት ወንድ ልጅና ባለቤታቸው በተንደላቀቀው መኖሪያ ቤታቸው አንዲት ጊኒያዊት ወጣት ለአሥራ ስድስት ዓመታት በባርነት ይዘው አኑረዋል ተብለው በዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ፍ/ቤት ክስ ተመሰረተባቸው።

መሐመድ ቱሬ እና ዴኒስ ክሮስ ቱሬ የውጭ ሀገር ሰውን በግዴታ በማሰራትና ለገንዘብ ጥቅም ብሎ በማስቀመጥ ወንጀል ተከሰዋል። የተከሳሾቹ ጠበቃ ክሱ የፈጠራ ውንጀላ የተሞላበት ነው ሲሉ ውድቅ አድርገዋል። ከሳሽ አቃቤ ህጉ በበኩላቸው ባልና ሚስቱ ማንነቷ ያልተገለፀውን ሴት ልጅ ከጊኒ መንደርዋ እኤአ በ2000 ወደዩናይትድ ስቴትስ እንዳመጧት ገልፀዋል።

ከሁለት ዓመታት በፊት በጎረቤቶች ዕርዳታ አምልጣ ወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማኅበር /ወሴክማ/ ተወስዳ እንድትኖር መደረጉ ተዘግቧል። “ከጥዋት እስከማታ በምግብ ሥራ፣ በፅዳት እና በልጆች ጥበቃ ሲያሰሩኝ ነበር” ስትል ወጣቱዋ ቃሏን ሰጥታለች። ጎረቤቶቹ ልጅቱ ቤቱን ቀለም ስትቀባ፣ የጓሮ አትክልቶች ሣር ስትቆርጥ አይተናል ብለዋል። ትምህርት ቤት እንዳላስገቧት ደሞዝ እንዳልከፈሏት ገልፃለች። በኮረንቱ ገመድና በቀበቶ ይደበድቡኝ ነበር አንድ ጊዜ ከጆሮዬ ላይ ጉትቻ መንጭቀው አውልቀው አቁስለውኛል ስትል ተናግራለች። ተከሳሾቹ ይቀድሞ የጊኒ መሪ ልጅ ባለቤታቸው በወንጀሉ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ሰላሳ ዓመት እስራትና አምስት መቶ ሺህ ዶላር ቅጣት ያስፈርድባቸዋል። መሃመድ ቱሬ ጊኒ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛትነት በ1958 ነፃ ስትወጣ የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት የነበሩት አህመድ ሴኩ ቱሬ ልጅ ናቸው፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG