ዋሺንግተን ዲሲ —
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በዓመታዊው የአዲስ ዓመት መልዕክታቸው ዘመኑ የሰላምና ብልጽግና እንዲሆን ተመኝተው ከደቡብ ኮሪያ ጋር የተሻለ ግንኙነት እንደሚኖርም አስታወቁ።
አንዳንድ የሰሜን ኮሪያ ነዋሪዎች፣ ባለፈው 2018 ያልተሳካውን ከደቡብ ኮሪያ ጋር እንዲኖር የሚመኙትን ግንኙነት ፕሬዚዳንቱ ዕውን እንዲያደርጉትም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
“ለታላቂ መሪ” በሚል በመተቋቋመው የአቀባበል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ኪም ሱ ከኡን ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የደቡብ ከሪያ ዜጎች ሥራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ