በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከካናዳ፣ ከሜክሲኮና ከዩናይትድ ስቴትስ የተውጣጡ ከፍተኛ የንግድ ተወካዮች ጉባዔ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ከካናዳ፣ ከሜክሲኮና ከዩናይትድ ስቴትስ የተውጣጡ ከፍተኛ የንግድ ተወካዮች፣ በእንግሊዝኛው ምኅፃረ ቃል /NAFTA/ ስለሚባለው ስለ ሰሜን አሜሪካው ነፃ የንግድ ሥምምነት ለመደራደር ዛሬ ሰኞ መሰባሰባቸው ተሰማ።

ሦስቱ ሀገሮች ድርድሩን እአአ ባለፈው 2017 ለማጠናቀቅ አቅደው፣ ነገር ግን የተለያዩ ሀገሮች ባነሷቸው ጉዳዮች ምክንያት ቀኑ መጓተቱ ታውቋል።

በቅርቡ ሞንትሪያል ላይ የተካሄደው ስብሰባ፣ በተሽከርካሪ ኢንዱስትሪ ላይ በተላለፉ የክርክር ውሳኔዎች ላይ የተነሱ ጥያቄዎች ታክለው ቀርበው እንደነበር ታውቋል።

እናም በዛሬው ድርድር ውጤት ይገኛል የሚል አዎንታዊ ግምት ያለ ቢሆንም፣ በካናዳ በኩል ግን ብዙ መሠራት እንዳለበት ታውቋል።

የካናዳው ዋና ተደራዳሪ ወኪል ስቲቨ ቨርሁለ ባለፈው ቅዳሜ በተናከሩት ቃል፣ በተቻለ መጠን ወደ አዎንታዊ ውጤቱ ነው እያዘነበልን ያለንው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG