በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በናይጀሪያ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ናይጀሪያ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ብዛት፣ እየጨመረ በሄደበት በአሁኑ ወቅት፣ ታማሚዎቹ ከማኅበረሰቡ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ተከታትሎ የማግኘቱ ጥረት ከባድ እንደሆነባቸው፣ የጤና ባለሥልጣኖች ተናገሩ።

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት የመሰረቱት፣ የኮቪድን ጉዳይ የሚያስተባብረው ግብረ ኃይል፣ በሽታው ላይ ያለውን አመለካከት በመጥቀስ፣ ንክኪን የሚከታተሉትን ሰዎች የማይረዱትን ነቅፏል።

በአንዳንድ ማኅበረሰቦች ግን፣ የአካባቢ መሪዎች፣ ንክኪን የሚከታተሉትን ሰራተኞች ለመርዳት መነሳታቸው ተገልጿል።

ናይጀሪያ 42,208 የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች ያሏት ሲሆን 19ሺህ ሰዎች ማገገማቸውንና 873 መሞታቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል መረጃ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG