በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ ዙሪያ በተካሄደ የአካባቢ ምርጫዎች አራት ሶማሌ-አሜሪካውያን አሸነፉ

በመካከለኛው ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የሜነሶታ ክፍለ ግዛት የሚኒያፖሊስ ከተማ እአአ 2013 በምክር ቤት አባልነት በመመረጥ የመጀመሪያው ሶማሊያዊ-አሜሪካዊ አብዲ ዋርሳሜ ተፎካካሪያቸውን ሞሃመድ ኑርን ሃምሳ ለአርባ ሰባት በመቶ በሆነ ጠባብ ልዩነት በማሸነፍ ነው በድጋሚ የተመረጡት።

በመካከለኛው ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የሜነሶታ ክፍለ ግዛት የሚኒያፖሊስ ከተማ እአአ 2013 በምክር ቤት አባልነት በመመረጥ የመጀመሪያው ሶማሊያዊ-አሜሪካዊ አብዲ ዋርሳሜ ተፎካካሪያቸውን ሞሃመድ ኑርን ሃምሳ ለአርባ ሰባት በመቶ በሆነ ጠባብ ልዩነት በማሸነፍ ነው በድጋሚ የተመረጡት።

“ከጥር ወር አንስቶ ሁኔታችን መልካም ነበር። አሁን ደግሞ በምርጫው አሸነፍን። በእጅጉ ተደስቻለሁ።” ብለዋል ዋርሳሜ የምርጫውን ውጤት ካረጋገጡ በኋላ በሰጡት አስተያየት።

በሁለተኛው የምክር ቤት አባልነታቸው ዘመናቸው በምርጫው ካሸነፉ በሶማሊያዊ-አሜሪካውያን ማኅበረሠባቸው እና በፖሊስ መካከል ያለውን ግንኙነት በማሻሻል እንደሚሰሩ የተናገሩት ዋርሳሜ የሶሜሌ ተወላጆት መገበያያ አዳራሽ እንዲገነባ በሚል ያላቸውን ውጥን አስተዋውቀዋል።

አቡዱልቃዲር ሃሰን የተባለ ወጣት ሶማሊያዊ-አሜሪካዊም ለሚኒያፖሊስ ከተማ የፓርክ እና መዝናኛ አገልግሎቶች ቦርድ አባልነት ሲመረጥ፣ ፋርቱን አህመድ ከሚኒያፖሊስ በስተምዕራብ በምትገኘው የሆፕኪንስ ከተማ የትምሕርት አስተዳደር ቦርድ አባልነት ተመርጠዋል።

በዋሽንግተን ክፍለ ግዛቷ የቱክዊላ ከተማም ዛክ ኢዳን የተባሉ ሌላ ሶማሊያዊ-አሜሪካዊ ለሠላሳ ስድስት ዓመታት በምክር ቤት አባልነት ያገለገሉትን አንጋፋ አባል በመተካት አዲሱ አባል ሆነው ተቀላቅለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG