በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ አዲስ ገንዘብ እንድታትም ዓለምቀፍ የገንዘብ ድርጅት ጥረት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ሶማሊያ ይህ የአውሮፓውያን ዓመት ከማብቃቱ በፊት አዲስ ገንዘብ እንድታትም በዓለምቀፍ የገንዘብ ድርጅት የተመራ ጥረት እየተካሄደ መሆኑን የሃገሪቱ የገንዘብ ሚኒስትር ተናገሩ።

ሶማሊያ ይህ የአውሮፓውያን ዓመት ከማብቃቱ በፊት አዲስ ገንዘብ እንድታትም በዓለምቀፍ የገንዘብ ድርጅት የተመራ ጥረት እየተካሄደ መሆኑን የሃገሪቱ የገንዘብ ሚኒስትር ተናገሩ።

ሚኒስትሩ አብዲራህማን ዱዋሌ ቤይሌህ ከቪኦኤ የሶማሊኛ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ /IMF/ ከመንግሥታችን ጋር ለመሥራት ፈቃደኛ ሆንዋል፣ ዓለምቀፍ የገንዘብ ድርጅት ገንዘቡን ከሚያመጣበት አምጥቶ ሊረዳን ዝግጁ ሆኗል፣ ሌሎችም ምንጮች ሊኖሩን ቢችሉም እኛ ግን በ/IMF/ በኩል እንሠራለን ብለዋል።

የሶማሊያ መንግሥት ለዚህ ጉዳይ አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ገልጸው ግማሹ በቀጥታ የአዲሱን ገንዘብ ኖቶች ለማተም ቀሪው ግማሹ ደግሞ ገንዘቡ ሥራ ላይ ሲውል ዋጋውን እንዳይዋዥቅ ለማድረግ እንደሚውል ገልፀዋል።

የሶማሊያ ማዕከላዊ ባንክ እኤአ ከ1991 ወዲህ በደምብ ሰርቶ አያውቅም።

የድሮው ገንዘቧ ጠፍቷል ወይም ኖቶቹ አርጅተው፣ ተበጫጭቀዋል በመሆኑም የንግድ ልውውጡ የሚካሄደው በአሜሪካ ዶላር ነው። ወይም ደግሞ አብዛኛው የውሸት የሆነ ገንዘብ እትመው የሚያሰራጩም አሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG