በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እውቅና የሚሹት የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ዩናይትድ ስቴትስን ጎብኝተው ተመለሱ


የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ
የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ

ራሷን በሉዓላዊ አገርነት የሰየመችው ሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት አገራቸው እንድታገኝ የሚሹትን እውቅና ሳያገኙ በዩናይትድ ስቴትስ የሚያደርጉትን ጉብኘት አጠናቀው መመለሳቸው ተነገረ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ግን ጉዟቸውን የተሳካ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ለቪኦኤ የሶማልኛው ክልፍ ሲናገሩ “ለኛ ዋናውና አስፈላጊው ነገር ከሰዎች ጋር እንደሶማሌ አካል ሆነን ሳይሆን እንደ ነጻና ሉዐላዊ አገር ሆነን እውቅና እንዲሰጡን መነጋገራችን” ነው ብለዋል፡፡

ከመጋቢት 4 ጀምሮ ወደ ዋሽንግተን የመጡት የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ወደ አገራቸው እስኪመለሱ ድረስ፣ አገራቸው እውቅና እንድታገኝ ለማግባባት ከዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፣ ከተባበሩት ድርጅት ኃላፊዎች፣ ከአግባቢዎችና የሲቪል ማህብረሰብ አባላት መሪዎች ጋር መነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡

ዋይት ኃውስና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንድነቷ ለተጠበቀች ሶማልያ ያላቸውና ቁርጠኝነት ገልጸው ይሁን እንጂ ከሶማሌ ላንድ ጋር ጠንካራ ግንኙነት መመስረት የሚሹ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሞሊ ፊ መጋቢት 4 ባወጡት የትዊት መልዕክት “በአንድ ሶማሊያ” ፖሊሲ ማዕቀፍ ስር፣ ከሶማሌ ላንድ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር ለመነጋገር መቻላችንን በደስታ እንቀበለዋለን ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG