በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከበርበራ ኢትዮጵያ ጎዳና


በርበራ ወደብ፤ ሶማሊላንድ
በርበራ ወደብ፤ ሶማሊላንድ

የሶማሊላንዷን የወደብ ከተማ በርበራን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኝ አውራ ጎዳና ሊሠራ ነው።

ሰሜን ምዕራባዊቱን ተገንጣይ ክልል የባሕር እንቅስቃሴዎች መናኸሪያ ሊያደርጋት ይችላል የተባለው መንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ የመሠረት ደንጊያ ባለፈው ሣምንት ተጥሏል።

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ መሠረቱን ያኖሩበት ሥነ-ሥርዓት የተከናወነው ዋና ከተማዪቱ ሃርጌሳ ውስጥ ሲሆን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ ከማልና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የዱባዩ የወደብ ላይ አገልግሎቶችና አቅርቦቶች ድጋፍ ሰጭ ኩባንያ ዲፒ ወርልድ ባለሥልጣናትም ተገኝተዋል።

111 ሚሊየን ዶላር እንደሚፈጅ የተነገረለት የበርበራ ሲቪል አይሮፕላን ጣቢያ ግንባታን የሚያካትተው ፕሮጀክት በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑን የሶማሊላንድ የትራንስፖርትና መንገዶች ልማት ሚኒስትር አብዱላሂ አቦኮር ኦስማን ተናግረዋል።

ከበርበራ ወደብ ኢትዮጵያ ድንበር የሚያደርሰው አውራ ጎዳና 245 ኪሎ ሜትር የሚሠራው ከአስፋልት ጋር ተመሣሣይ በሆነ ታርማክ ሲሆን 21 ኪሎሜትር ተላላፊና የማቆራረጫ መንገዶችንና ሰባት ድልድዮችን የሚያካትት እንደሆነ ታውቋል።

ይህ የበርበራ-ኢትዮጵያ መንገድ ግንባታ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ፣ በሶማሊላንድና በዲፒ ወርልድ መካከል በአመዛኙ በርበራ ወደብን ለማዘመን በሚል የተፈረመ ለሰላሣ ዓመታት የሚዘልቅ የ442 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት አካል ነው።

አዲሱ የበርበራ ኮሪዶር ያለማቋረጥ የሚያድገውን የኢትዮጵያን ወጭ ንግድ ለማቀላጠፍ የሚያግዝ ከመሆኑ በተጨማሪ የራሷ የባሕር በር የሌላትን የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ሃገር ኢትዮጵያን ከጂቡቲ ወደብ ብቸኛ ጥገኛነት ለማላቀቅ የሚያስችል አማራጭ እንዲኖራት እንደሚያደርግ የአካባቢው የምጣኔ ኃብት ኤክስፐርቶች ይጠቁማሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ከበርበራ ኢትዮጵያ ጎዳና
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:43 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG