በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስት የአልሸባብ አማፅያን በጁባ ክልል ጂሊብ ተገደሉ

አንድ የአፍሪካ ዕዝ ያወጣው መግላጫ ትላንት በመካከለኛው ጁባ ክልል በምትገኘው ጂሊብ ከተማ ላይ በተከፈተው ጥቃት ሦስት የአልሸባብ አማፅያን ተገድለው ከባድ መሣርያ የደገነ ተሽከርካሪ ተድምስሷል ይላል።

አንድ የአፍሪካ ዕዝ ያወጣው መግላጫ ትላንት በመካከለኛው ጁባ ክልል በምትገኘው ጂሊብ ከተማ ላይ በተከፈተው ጥቃት ሦስት የአልሸባብ አማፅያን ተገድለው ከባድ መሣርያ የደገነ ተሽከርካሪ ተድምስሷል ይላል።

በጥቃቱ የተጎዱ ሲቪሎች እንደሌሉ የአፍሪካ ኮማንድ ገልጿል።

የአከባቢው ነዋሪዎች በገለፁት መሰረት የተደምሰሰው ተሽከርካሪ “ዙ” የተባለ በሶቭያት ኅብረት ዘመን የተሰራ ፀረ አይሮፕላን መሣርያ ነበር የደገነው።

የአፍሪካ ኮማንድ ወይም ዕዝ በአልሸባብ ላይ ሥምንት ጥቃቶች ማካሄዱን ተናግሯል። የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በቅርብ የሚከታተሉ ጠበብት ግን የአፍሪካ ዕዝ ሦስት ተጨማሪ ጥቃቶች ማካሄዱን መዝግበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG