በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ በጸጥታው ምክር ቤት አፍሪካን በመወከል ተመረጠች


ፎቶ ፍይል፦ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት
ፎቶ ፍይል፦ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት

ዴንማርክ፣ ግሪክ፣ ፓናማ፣ ፓኪስታን እና ሶማሊያ እኤአ ከ2025 እስከ 2026 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ያልሆኑ አባላት በመሆን ጠቅላላ ጉባኤው በሰጠው ድምጽ ተመርጠዋል፡፡

ሶማሊያ ሞዛምቢክን በመተካት የአፍሪካ ሀገራትን ቡድን መቀመጫ ትወስዳለች፡፡

የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አህመድ ሙአሊም ፊቂ ከድምጽ አሰጣጡ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “በተሳትፏችን የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ፣ በፀጥታው ምክር ቤት እና በቀጠናው ድርጅት መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንጥራለን።” ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም “ሶማሊያ የዓለማችንን ውስብስብ ጉዳዮች ለመፍታት ውጤታማ የሆነ የባለብዙ ወገንተኝነት እና ትብብር ማዕከላዊ ሚናን ትገነዘባለች።” በማለት ተናግረዋል፡፡፡

ፓኪስታን ለኤዥያ-ፓሲፊክ ቡድን የጃፓንን መቀመጫ ስትረከብ ከጥር ወር ጀምሮ ደግሞ ፓናማ የላቲን አሜሪካ እና የካሪቢያንን ቡድን በመወከል በኢኳዶር የተያዘውን መቀመጫ ትቀበላለች፡፡

ዴንማርክ እና ግሪክ ለምእራብ አውሮፓ እና ሌሎች የተመደቡ ቦታዎችን በመያዝ በታህሳስ ወር ማልታ እና ስዊዘርላንድን ይቀይራሉ፡፡

አዲሱ የሁለት ዓመት የፀጥታው ምክር ቤት የቆይታጊዜ እኤአ ጥር1 2025 ይጀምራል ጀምሮ ታህሳስ 31 ቀን 2026 ያበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG