በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግሥታቱ ድርጅት “የሶማልያ ወታደሮች ትግራይ ውስጥ መኖራቸውን” ገለጸ


ልጆቻችን በትግራይ ግጭት ውስጥ ተሳትፈዋል ያሉት ሴቶች በዛሬው እለት ሞቃዲሾ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል፡፡
ልጆቻችን በትግራይ ግጭት ውስጥ ተሳትፈዋል ያሉት ሴቶች በዛሬው እለት ሞቃዲሾ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል፡፡

ወደ ኤርትራ ለሥልጠና ተልከው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማልያ ወታደሮች በኢትዮጵያ ትግራይ ውስጥ በተደረገው ውጊያ ተካፋይ ሆነዋል በሚል፣ በዚህ ሳምንት በወጣው ሪፖርት የተነሳ፣ በሶማልያ መንግሥት ላይ የሚደረገው ግፊት እያየለ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

የልጆቻቸው አድራሻ የጠፋባቸው የወታደሮቹ ቤተሰቦች ፈርማጆ ተብለው የሚጠሩትን የሶማልያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ መሀመድን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን እሳቸው ግን ሪፖርቱን አስተባብለዋል፡፡

የቪኦኤ ዘጋቢ መሃመድ ካዬ ከሞቃድሾ እንደዘገበው ደግሞ የተወካዮቹ ምክር ቤት ኮሚቴ የወታደሮችን አድራሻ በሚመለከት ምርመራ እንዲደረግ ጥያቄ ማቅረባቸው ተነግሯል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የሰአብአዊ መብት ጉባኤ በዚህ ሳምንት የወጣው ዘገባ እንዳመለከተው “ለሥልጠና ወደ ኤርትራ ተልከው የነበሩ ወታደሮች በኢትዮጵያው የትግራይ ውጊያ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡”

የሶማልያ መንግሥት ግን ወታደሮቹ ትግራይ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን አስተባብሏል፡፡

ፉስ ዋርዴር ከሶማልያ መንግሥት ምላሽ ከሚጠባበቁ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ወላጆች መካከል አንዷ ናቸው፡፡ የ22 ዓመት ልጃቸው ሲድ አሊ አብዲ ወደ ኤርትራ ለሥልጠና ከተላኩ ወታደሮች መካከል አንዱ ነው፡፡

ልጃቸው ወደ ኤርትራ የሄደው ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ ነው፡፡ እስከዚህ ዓመት ጥር ወር ድረስ ከሱ የሰሙት ምንም ነገር የለም፡፡ ባላፈው ሳምንት እንደገና የደወለላቸው ሲሆን ለህይወቱ በጣም የፈረሉት በመሆኑ የልጃቸውን ደህንነት ማረጋገጥ በሰላም ወደ ቤቱ እንዲመለስ ማድረጉ የባለሥልጣናቱ ኃላፊነት መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ከቤተሰቦችና ከተቃዋሚ መሪዎች ጥያቄዎች የቀረቡ ቢሆንም የሶማልያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አቡዱላሂ ፎርማጆ ስለ ወታደሮቹ ምንም አስተያየት አልሰጡም፡፡

በፓርላማው የውጭ እና ዓለም አቀፉ ጉዳዮች ኮሚቴ ምንም ዓይነት ምላሽ ስላላገኘው ጥያቄ የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥበት ሁለት ደብዳቤዎች መላኩ ተመልክቷል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት “የሶማልያ ወታደሮች ትግራይ ውስጥ መኖራቸውን” ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:20 0:00

ትልቅ ስልጣን ያለው የምክር ቤቱ ኮሚቴ መሀመድ ሀሰን እድሪስ የአገሪቱ የደህንነት ጉዳዮች በሆነው ጉዳይ ላይ ፕሬዚዳንቱ ኃላፊነት መውሰድ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

እንዲህ ብለዋል መሀመድ

ጉዳዩ ያሳሰበን መሆኑን በመግለጽ ፕሬዚዳንቱ ወደ ኤርትራ ለሥልጠና የተላኩ ወታደሮች በኢትዮጵያው ትግራይ እንዲሰማሩ ተደርገዋል ስለሚለው ክስ በግልጽ ወጥተው ምላሻቸውን እንዲሰጡ ጠይቀናል፡፡ ምንም እንኳ ሁለት ደብዳቤዎችን ብንልክም፣ በየእለቱ የሚደረገውን የወታደሮቹን ቤተሰቦች ተቃውሞ ጨምሮ በቃልም የተጠየቁ ቢሆንም፣ እንዳለመታደል ሆኖ ፕሬዚዳንት ፎርማጆ ግን እስካሁን ድረስ በግልጽ ወጥተው አድራሻ ጠፍቷል ስለተባለው ወታደሮች የተናገሩት ነገር የለም፡፡ ዝም ማለት ነው የመረጡት፡፡ በጣም የሚረብሽ ሁኔታ ነው ያለው፡፡

እኤአ ሰኔ 2018 ሶማልያ፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ፣ የደህንነት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የደህንነትና ጉዳዮች ተናታኝ እና የቀድሞ የሶማልያ ብሄራዊ ደህንነትና የመረጃ ድርጅት ምክትል ድሬክተር የነበሩ አብዲሰላም ጉሌ ፣ሁኔታውን በቅርበት ተከታትለዋል፡፡

እሳቸው እንደሚሉት ትግራይ ውስጥ የተገደሉት የሶማልያ ወታደሮች ምን ያህል እንደሆኑ ግልጽ አይደለም፡፡ እንዲህ ብለዋል

“በሥልጠናው ወቅትም ሆነ ከኤርትራ ወታደሮች ጋር ተሰልፈው በትግራይ ውጊያ ከተሳተፉት ውስጥ ስንት ሰዎች እንደሞቱ አናውቅም፡፡ ትክክለኛውን ፋይል እስካለገኘን ድረስ፣ ድፍን ያለ ጨለማ ነገር ነው፡፡ምን ያህል ወታደሮች እንደተላኩ ምን ያህሎቹ እስካሁን በህይወት እንዳሉ ለማረጋገጥ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለዚህ ትክከለኛውን ቁጥር ማወቅ እነዚህ ጠፍተዋል የተባሉትን ወታደሮች ለማወቅ በጣም አስፈላጊና ቁልፍ ነገር ነው፡፡”

XS
SM
MD
LG