በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጋዜጠኞች በመገደል ሶማልያ በአንደኛነት ትፈረጀች

Mourners pray over the bodies of journalists Mohamed Abdikarim Moallim Adam, a reporter for the London-based Universal television, and Abdihakin Mohamed Omar, a producer for the Somali Broadcasting Corporation, at their funeral in Mogadishu, Somalia, July

የጋዜጠኞች መገደል ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ምስጢር የሆነባት ሀገር ከመላው ዓለም ሶማልያ በአንደኛነት ትፈረጃለች ሲል፣ ለጋዜጠኞች መብት መጠበቅ የቆመው ኮሚቴ ሲፒጄ አስታወቀ።

የጋዜጠኞች መገደል ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ምስጢር የሆነባት ሀገር ከመላው ዓለም ሶማልያ በአንደኛነት ትፈረጃለች ሲል፣ ለጋዜጠኞች መብት መጠበቅ የቆመው ኮሚቴ ሲፒጄ አስታወቀ።

ኮሚቴው ዛሬ ማስከኞ ባወጣው 10ኛ ዓመታዊ /ግልባል ኢሚዩኒቲ ኢንዴክስ/ ማለት ጋዜጠኞችን የጥቃት ዒላማቸው የሚያደርጉ ቡድኖችን በሚያሳየው ሰንጠረዥ ላይ እንዳመለከተው፣ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ፣ የተራዘመ የርስ በርስ ጦርነት በቀጠለባት ሶማልያ፣ ከ24 በላይ የሆኑ ጋዜጠኞች አሟሟት ምስጢራዊ ሆኖ ቆይቷል።

ባለፈው ዓመት በ3ኛነት የተፈረጀችው ሦርያ በአሁኑ ዓመት 2ኛ መሆኗን ያመለከተው ሲፒጄ፣ ጋዜጠኞች እየተገደሉ ገዳዮቻቸው በነፃ የሚለቀቁባት ሀገር ሆናለችም ብሏል።

ኢራቅ ፫ኛ ነች። ኢራቅ ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች ከእስላማዊ ነውጠኞች፣ መንግሥት ከሚደግፋቸው ሚሊሽያዎችና ከሌሎችም ቡድኖች ወከባና እንግልት ይደርስባቸዋል።

በፖለቲካ ተቀናቃኞች መካከል እኤአ2015 በነበረው ውዝግብ 5 ጋዜጠኞች የተገደሉባት ደቡብ ሱዳን፣ በሰንጠረዡ 4ኛ ረድፍ ላይ ተቀምጣለች።

የመንግሥት ባለሥልጣናትና ወንጀለኞች ጋዜጠኞችን እየገደሉ ያለ ምንም ቅጣት በነፃነት የሚንቀሳቁባት ፊሊፒንስ 5ኛ ላይ ነች።

በዚሁ በሲፒጄ ሰንጠረዥ ውስጥ፤ የዴሞክራሲ አምባሳደር የሚያደርጉት ብራዚል፣ ህንድ፣ ሜክሲኮና ሩስያም የተካተቱ መሆናቸው ተመልክቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG