በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቀልቢ ዻጋ ለኢትዮጵያ ተሰጥተዋል


የሶማሊያ መንግሥት የኦጋዴን ነፃነት ግንባር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ቀልቢ ዻጋ ተብለው የሚጠሩትን አብዲሃኪም ሼህ ሙሴን ለኢትዮጵያ አሳልፎ መስጠቱን አውግዞ ዓለምአቀፍ ጣልቃገብነት ጠይቋል።

የሶማሊያ መንግሥት የኦጋዴን ነፃነት ግንባር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ቀልቢ ዻጋ ተብለው የሚጠሩትን አብዲሃኪም ሼህ ሙሴን ለኢትዮጵያ አሳልፎ መስጠቱን አውግዞ ዓለምአቀፍ ጣልቃገብነት ጠይቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥትም የተጠቀሱት የቡድኑ መሪ በእጁ እንደሚገኙ አረጋግጧል።

በሌላ በኩል ደግሞ የሶማሊያ ባለሥልጣናት ስለ አብዲሃኪም ሼህ ሙሴ ለኢትዮጵያ ተላልፎ መሰጠት ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

አብዲሃኪም ሼህ ሙሴ ማዕከላዊቱ ሶማሊያ ከተማ ጋልካአዮ ውስጥ በሃገሪቱ የደኅንነት ሠራተኞች የተያዙት ባለፈው ሣምንት ረቡዕ፤ ነኀሴ 17/2017 ዓ.ም. እንደነበረ የግንባሩ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮምዩኒኬሽንና የኢንፎርሜሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ቀልቢ ዻጋ ወይም አብዲሃኪም ሼህ ሙሴ ጋልካአዮ ከተማ ውስጥ ለሁለት ቀናት ተይዘው ከቆዩ በኋላ ወደ ዋና ከተማዪቱ ሞቃዲሾ መወሰዳቸውንና ሰኞ፤ ነኀሴ 22/2009 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ተላልፈው መሰጠታቸውን አቶ ሃሰን ገልፀዋል።

የአብዲሃኪም ሼህ ሙሴን ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፎ መሰጠት አስመልክቶ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር ባወጣው መግለጫ የሶማሊያን ከፍተኛ መሪዎች ከፕሬዚዳንቱ ጀምሮ በስም እየጠራ “በሶማሌ መንግሥት ላይ ብሄራዊ ወንጀል ፈፅመዋል” ሲል ከስሷል።

በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ አብዲሃኪም ሼህ ሙሴ ተላልፈው እንደተሰጧቸው አረጋግጠው የተፈለጉት የኢትዮጵያ መንግሥት “የሽብር ቡድን” ብሎ የፈረጀው ቡድን መሪ በመሆናቸው መሆኑንና የሶማሊያ መንግሥትም አሳልፎ የሰጣቸው በመንግሥታቱ መካከል ባለ ስምምነት መሠረት መሆኑን አመልክተዋል።

ሞቃዲሾ ላይ በብሄራዊው ቤተመንግሥት ቪላ ሶማሊያ ውስጥ ትናንት ምሽት ላይ መግለጫ የሰጡት የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ኻይሬና የሃገሪቱ ብሄራዊ ደኅንነት ኃላፊ አብዱላሂ ሞሐመድ አሊ (ሳንባሎልሼ) የአብዱሃኪምን ተላልፎ መሰጠት ከማረጋገጥ የዘለለ ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ቀልቢ ዻጋ ለኢትዮጵያ ተሰጥተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:17 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG