ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረቱ ዘማች ኃይል - አሚሶም በቅርቡ ከአልሻባብ አስለቅቆ የያዛት ዑዱር ከተማ በአማፂያኑ ተዋጊዎች የተከበበች መሆኑን የባኩል ክልል አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገለፁ፡፡
በከተማይቱ ውስጥ ያለው የሕይወት ሁኔታም በጣም ከባድ መሆኑን የክልሉ አስተዳዳሪ ሞሐመድ አብዲ ቶል አመልክተዋል፡፡
ዑዱር የተያዘችው በሶማሊያ መንግሥት ኃይሎችና የአሚሶም አካል በሆኑት የኢትዮጵያ ወታደሮች መሆኑ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሶማሊያ ውስጥ የሚታየው ወታደራዊ ሁኔታ የሚያበረታታ መሆኑን በሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ልዩ ተወካይ ኒኮላስ ኬይ ተናግረዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡