ሞቅዲሾ ከተማ ውስጥ ትናንት ማክሰኞ የደረሰው የአጥፍቶ-ጠፊዎች ፍንዳታ፣ በረሀብና ድርቅ በተመታችው አገር አብዛኛውን ክፍል የተቆጣጠሩት የአል-ቃዒዳ ርዝራዦች መዳከማቸውን የሚያሳይ ድርጊት ነው ሲሉ፣ የሶማልያው ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።
በፍንዳታው ቢያንስ 70 ሰዎች ተገድለው ብዙዎች ቆስለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሞቅዲሾ ውስጥ የተፈጸመው የትናንቱ የአጥፍቶ ጠፊዎች ፍንዳታ፣ ሶማልያ ውስጥ የሚካሄደውን የድርቅና የረሀብ ማስወገድ ጥረቶችን አያደናቅፈውም ስትል ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች።
ከዚህ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴቢድ ጎለስት እንደዘገበው ደግሞ፣ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ የእርዳታ ቡድን የሶማልያውን የሰብዓዊ አቅርቦት ሁኔታ ለመገምገም ወደ ክልሉ አምርቷል።
የሶማልያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብዲዌሊ ሞሐመድ አሊ እንደተናገሩት ሞቅዲሾ ውስጥ በሚገኘው የትምህርት ሚኒስቴር ደጃፍ ላይ ትናንት፤ ማክሰኞ አጥፍቶ ጠፊዎች ያደረሱት ፍንዳታ የሽግግር መንግሥታቸው፣ አልቃዒዳን ለመደምሰስ ያሳለፈውን ውሣኔ ቁጥርጠኛነት የሚያረጋግጥ ነው።
እነዚህ ፈሪዎች ይበልጥ ተደራጅተው ተጨማሪ የፈሪ ዱላቸውን ሲያነሱ በዝምታ ልናያቸው አንችልምና፣ ጣልቃ ገብተን የምናስቆምበት ወቅቱ አሁን ነው። አብዛኛዎቹ ሰለባዎች፣ የነፃ ትምህርት ፈተና ውጤታቸውን ለመስማት በትምህርት ሚኒስቴር አካባቢ የተሰባሰቡ ተማሪዎችና የእነርሱ ቤተሰቦች ናቸው።
ዝርዝሩን ከከተማው ያዳምጡ