በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አልሸባብ አንድ የእንግሊዝ ዜጋን ጨምሮ አምስት ወንዶችን ረሸነ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የሶማሊያው ፅንፈኛ ቡድን አልሸባብ አንድ የእንግሊዝ ዜጋን ጨምሮ አምስት ወንዶችን ረሸነ። ለዩናይትድ ስቴትስ ለእንግሊዝና ለሶማሊያ የደኅንነት ድርጅቶች ሥለላ ስታካሂዱ ነበር ብሎ ወንጅሏቸው መሆኑ ታውቋል።

የሶማሊያው ፅንፈኛ ቡድን አልሸባብ አንድ የእንግሊዝ ዜጋን ጨምሮ አምስት ወንዶችን ረሸነ። ለዩናይትድ ስቴትስ ለእንግሊዝና ለሶማሊያ የደኅንነት ድርጅቶች ሥለላ ስታካሂዱ ነበር ብሎ ወንጅሏቸው መሆኑ ታውቋል።

ጂሊብ በምትባለው ከተማ ነው ትናንት ማክሰኞ የአልሸባብ ፍርድ ቤት ሰዎቹ እንዲገደሉ የወሰነባቸው።

ከተረሸኑት መካከል አንደኛው የሠላሳ ሁለት ዓመቱ መሐመድ አህመድ መሐመድ የሚባል የቢሪታንያ ዜጋ እንደሆነና ከለንደን ወደሶማሊያ ተጉዞ ቡድኑን የተቀላቀለ እንደነበር አልሻባብ ገልጿል።

አልሸባብ ሰውየውን ለእንግሊዝ የደኅንነት ድርጅት በመሰለልና በቡድኑ ውስጥ ያለ የእስላማዊ መንግሥት ቡድን ደጋፊ አንጃ መሪ ብሎ ከሦስት ዓመት በፊት እንዳሰረው ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG