በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የበረሃ አንበጣ በሶማሊያ


ሶማሊያን በሃያ አምስት ዓመት ባልታየ ደረጃ በወራት የበረሃ አንበጣ ብዙ ሺህ ሄክታር ላይ ያለ ሰብል አውድሟል።

የአንበጣ መንጋው ሶማሊያን አጎራባች ምስራቅ ኢትዮጵያ ባሉ አካባቢዎች ሰባ ሺህ ሄክታር ስፋት ያለው ሰብል ማውደሙን የተመድ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ገልጿል።

ያሁኑ የአንበጣ መንጋ ከቀደሙት የከፋ መሆኑን የገለፀው ድርጅቱ ኬንያ ኤርትራ ጅቡቲ ደቡብ ሱዳንና ሱዳንን ጨምሮ ወደሌሎች የአፍሪካ ቀንድ ሃገሮች ሊዛመትም እንደሚችል ነው ያመለከትው።

የኤፍኤኦ የአካባቢው አስተባባሪ ዴቪድ ፊሪ የአየር ሁናቴው ለአንበጣው መራባት አመቺ ሳይሆንለት እንዳልቀረ ጠቁመው፣ እስከሚመጣው መጋቢትና ሚያዝያ መራባቱን ሊቀጥል እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG