በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታዋቂው የሶማሊያ ጋዜጠኛ አብዲአዚዝ መሃሙድ ጉሌድ በቦምብ ጥቃት ተገደለ


በአጥፍቶ ጠፊ ለተገደለው የሶማሊያ ጋዜጠኛ የፀሎት ስርዐት ሲካሄድ
በአጥፍቶ ጠፊ ለተገደለው የሶማሊያ ጋዜጠኛ የፀሎት ስርዐት ሲካሄድ

አልሻባብን አጥብቆ በመንቀፍ የሚታወቀውዝነኛው የሶማሊያ ጋዜጠኛ አብዲአዚዝ መሃሙድ ጉሌድ በቦምብ ጥቃት ተገደለ።

የሶማሊያ መንግሥት ራዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኛው አብዲአዚዝ ይበልጡን በሚታወቅበት ስሙ አብዲአዚዝ አፍሪካ ትናንት ቅዳሜ ሞቃዲሾ ውስጥ መኪና ውስጥ እንዳለ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ አፈንድቶ ገድሎታል።

የራዲዮ ጣቢያው ዳይሬክተር አብዲ አፍሪካ በጥቃቱ ሲገደል አንድ ሌላ ጋዜጠኛ መቁሰሉን የሶማሊያ ባለስልጣናት እና ባልደረቦቹ ገልጸዋል።

የሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቭዢን ስራ አስኪያጁ ሸርማርኬ ማህሙድ ዋርሳሜ በጽኑ መቁሰሉን የሶማሊያ መንግሥት ቃል አቀባይ ሞሃመድ ሙአሊሙ ተናግረዋል።

የፖሊሲ ቃል አቀባይ ስለጥቃቱ በሰጡት መግለጫ አጥፍቶ ጠፊው ጋዜጠኞቹ ወደነበሩበት መኪና ሮጦ ቦምቡን እንዳፈነዳባቸው አመልክተዋል። አልሻባብ ለጥቃቱ ሃላፊነት ወስዷል።

ጋዜጠኛ አብዲአዚዝ አፍሪካ ሞቃዲሾ ውስጥ በተለያዩ የግል ራዲዮ እና ቴሌቭዥን ጣቢያዎች ሲሰራ ቆይቶ በመንግሥቱ የራዲዮ እና ቴለቭዢን ጣቢያ ከአስራ ሁለት ዐመት በላይ ሰርቷል። ጋዜጠኛው ከአስር ዐመታት በላይ በተ መ ድ የሚደገፉትን የሶማሊያ ወታደሮችን መውጋታቸውን የቀጠሉትን ጽንፈኛ እስላማዊ ታጣቂዎች በግልጽ በመንቀፍ ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG