በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞቃዲሾ አንድ ጋዜጠኛ ተገደለ


ፎቶ ፋይል፦ ሞቃዲሾ
ፎቶ ፋይል፦ ሞቃዲሾ

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ ትናንት ሰኞ ማታ አንድ ጋዜጠኛ መገደሉ ተሰማ። ሰዒድ ዩሱፍ የተባለው ጋዜጠኛ ለሚባል ሞቃዲሾ የሚገኝ ካልሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ የሚሠራ እንደነበር የሶማሊያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ማኅበር አመልክቷል። ጋዜጠኛው ሞቃዲሾ ሆዳን ወረዳ ሴይ ቢያና በተባለ ሠፈር ጥቃት ያደረሰበት ግለሰብ በስለት ወግቶት ሆስፒታል እንደደረሰ ሕይወቱ ማለፉን ነው የማኅበሩ ዋና ፀሐፊ የገለፁት። ጥቃቱ በምን ምክንያት መነሻ እንደተፈፀመበት በግልፅ አልታወቀም፤ ኃላፊ ነኝ ያለም እስካሁን የለም ብለዋል።
ጋዜጠኛው የተጎደለው ትናንት ሰኞ በዓለም የፕሬስ ቀን ማግሥት መሆኑ ነው። ሶማሊያ ውስጥ የተሰማሩ ጋዜጠኞች በሥራቸው ምክንያት እጅግ ለከፋ አደጋ የተጋለጡ መሆናቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

XS
SM
MD
LG