በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ የአይሲስ ዕቅድ አውጪው ተገደለ


የሶማሊያ ካርታ
የሶማሊያ ካርታ

አሜሪካ በሶማሊያ የእስላማዊ መንግስት አሸባሪ ቡድን ላይ በምታካሂደው የአየር ጥቃት ዋና ዒላማ የነበረውና የሽብር ጥቃቶችን በማቀናበር የሚከሰሰው አህመድ ማሌኒኒኔ መገደሉ ታውቋል። ግለሰቡ ከአሥር ቀናት በፊት ጥር 24፣ 2017 ከሌሎች 13 ከፍተኛ የአይሲስ አመራሮች ጋራ መገደሉን የአሜሪካ ጦር የአፍሪካ ዕዝ ትላንት ማክሰኞ አስታውቋል።

አህመድ አሸባሪዎችን መልምሎ፣ በገንዘብ በመደገፍ ወደ አሜሪካ እና አውሮፓ ይልክ እንደነበር ከዕዙ የተገኘው መግለጫ አመልክቷል።

የአየር ድብደባዎቹን ውጤታማነት ለመገምገም ጊዜ መውሰዱን፣ ይህም ደግሞ የአካባቢው መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ ተራራማ በመሆኑ እንደሆነ እዙ አስታውቋል።

ድብደባው የተፈጸመው በሶማሊያ ጎሊስ ተራሮች፣ ካል ሚስካድ በተባለ ሥፍራ በርካታ ዋሻዎች ባሉበት አካባቢ እንደሆነም ተመልክቷል።

ድብደባው ቢያንስ አሥር ሥፍራዎችን ዒላማ ያደረገ እንደነበር አንድ የሶማሊያ መከላከያ አዛዥ በወቅቱ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG