በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ለሶማልያ አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠቱን እንደሚቀጥል የዋና ጸሐፊው ልዩ ተወካይ አረጋገጡ


በሶማሊያ ዐዲስ የተሾሙት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ልዩ ተወካይ ካትሪዮና ላንግ
በሶማሊያ ዐዲስ የተሾሙት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ልዩ ተወካይ ካትሪዮና ላንግ

በሶማሊያ ዐዲስ የተሾሙት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ልዩ ተወካይ ካትሪዮና ላንግ፣ በአገሪቱ ፌዴራላዊ ክልሎች የሚያደርጉትን ጉብኝት፣ በሂርሼቤሌ ክፍለ ግዛት ሲጀምሩ፣ ተመድ፣ ለሶማልያ አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠቱን እንደሚቀጥል፣ ለአገሪቱ ፕሬዝዳንት እንዳረጋገጡላቸው ገለጹ፡፡

ዐዲሱን ሥራቸውን ለመጀመር፣ በዚኽ ሳምንት ሶማሊያ የገቡት የዋና ጸሐፊው ልዩ ተወካይ፣ ከአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ ማሕሙድ እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሐምዛ አብዲ ባሬ ጋራ ተወያይተዋል፡፡

ከግዛቲቱ ፕሬዚዳንት ዓሊ አብዱላሂ ሑሴን ጋራ ባደረጉት ውይይት፥ ሰላም፣ ብልጽግና እና ደኅንነቷ ለተጠበቀ ሂርሸቢሌ ያላችሁን ምኞት ለማሳካት በጋራ እንሠራለን፤ ብለዋቸዋል፡፡

በክፍለ ግዛቷ የሰብአዊ ረድኤት ፍላጎቶች፣ በአካባቢ ጸጥታ እና በአገራዊ ጉዳዮች፣ ከፕሬዚዳንቱ ጋራ መነጋገራቸውንም፣ የመንግሥታቱ ድርጅት ልዩ ተወካዩዋ ገልጸዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ(OCHA) መረጃ መሠረት፣ ባለፈው ወር፣ በአካባቢው የደረሰው የጎርፍ አደጋ፣ በንብረት ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት ያደረሰ ሲኾን፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን አፈናቅሏል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል፣ ለፕሬዚደንቱ እንዳረጋገጡላቸው የገለጹት ልዩ ተወካዩዋ፣ “ነገር ግን፣ ችግሩን በዘላቂነት በመፍታት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል፤” ብለዋል፡፡

ከጸጥታ ጋራ በተያያዘ፣ በአል-ሻባብ ላይ እየተወሰደ ያለውን ርምጃ በተመለከተ፣ ፕሬዚዳንቱ ለልዩ ተወካዩዋ ማብራሪያ እንደሰጧቸው ገልጸዋል፡፡

“የተቆጣጠራቸውን አብዛኞቹን ቦታዎች ለማስለቀቅ ስለተካሔደው የተሳካ ዘመቻ ገለጻ አድርገውልኛል፡፡ አካባቢዎቹን ማረጋጋት፣ አስፈላጊ እንደኾነ ተነጋግረንበታል፡፡ የተመድን ድጋፍም አረጋግጬላቸዋለኹ፤” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG