በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ባንዣበበባት ቸነፈር ሳቢያ ትልቅ ቀውስ ይጠብቃታል ተባለ


በድርቅ ምክንያት ከገጠር አካባቢዎች የተፈናቅሉ የሶማሊያ ሴቶች እና ህጻናት መጠለያ ካምፕ ውስጥ የአልሚ ምግብ ድጋፍ ሊያገኙ ሲጠባበቁ፤ ባይዶዋ፣ ሶማሊያ፣ 9/12/2022
በድርቅ ምክንያት ከገጠር አካባቢዎች የተፈናቅሉ የሶማሊያ ሴቶች እና ህጻናት መጠለያ ካምፕ ውስጥ የአልሚ ምግብ ድጋፍ ሊያገኙ ሲጠባበቁ፤ ባይዶዋ፣ ሶማሊያ፣ 9/12/2022

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አጣዳፊ እርምጃ ካልወሰደ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሶማሊያውያን በድርቅ በተጠቃችው አገር ሊያልቁ ይችላሉ ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ።

"የቪኦኤዋ ሊሳ ሽላይን ከጀኒቫ እንደዘገበችው፣ በሶማሊያ እያንዳንዱ ዜጋ ረሃብ ተጋርጦበታል። ይህም ከአስር ዓመት በፊት ከታየውና ከሩብ ሚሊዮን ሰዎች በላይ ከጨረሰው ቸነፈር ወዲህ ከሁሉ የከፋ ነው" ሲል የዓለም የጤና ድርጅት አስጠንቅቋል።

በሶማሊያ የጤና ድርጅቱ ተወካይ ማሙኑር ማሊክ ከሞቃዲሺ እንደተናገሩት በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጦማቸውን ያድራሉ። በሶማሊያ ከሚገኙ ሕጻናት ገሚሱ ወይም 1.8 ሚሊዮን ያህሉ ደግሞ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል።

እነዚህ ህጻናት በአስቸኳይ ህክምና ካልተደረገላቸው ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ ብለዋል ተወካዩ።

“በአንዳንድ የጤና ጣቢያዎች በየሰዓቱ ህጻናት ሲሞቱ አይቻለሁ። ምግብና ውሃ ፍለጋ ረጅም ርቀት ተጉዘው የመጡ ናቸው። የደከመው አካላቸው የመጨረሻውን የጉዞ ርቀት መጨርስ አልቻለም” ብለዋል ማሊክ።

የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው፣ በሶማሊያ ከአሥር ሕጻናት አንዱ በቀላሉ መከላከል በሚችል በሽታ ሳቢያ ወደ ጤና ጣቢያ ይመጣል። ከሰባት ሕጻናት አንዱ ደግሞ እንደ ኩፍኝና ኮሌራ ያሉ ገዳይ ከሆኑ በሽታዎችን መከላከል የሚያስችለውን ህይወት አድን ክትባት ሳይወስድ ይቀራል።

ኃላፊው እንዳስጠነቀቁት፣ በወቅቱ መፍትሄ ካልተሰጠ ብዙ ሕጻናት ከረሃብ እና ከተመጣጠነ ምግብ እጦት ይልቅ በበሽታ ያልቃሉ።

XS
SM
MD
LG