በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሀገሪቱን አዋርደዋል ያላቸውን የአትሌቲክስ ሃላፊ አገደ


ናስሮ አቡካር አሊ
ናስሮ አቡካር አሊ

በአንድ ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ “ስፖርተኛ አይደለችም” የተባለች ተወዳዳሪ መሳተፏን የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋት መሠራጨቱን ተከትሎ፣ የሶማሊያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሀገሪቱን አዋርደዋል በሚል የአትሌቲክስ ሃላፊውን አግዷል።

የሶማሊያው የስፖርት ሚኒስትር ሞሃመድ ባሬ ሞሃመድ ትናንት እንዳስታወቁት፣ በቻይና በመካሄድ ላይ ባለው የበጋ የዩኒቨርሲቲዎች አትሌቲክስ ውድድር ላይ በ100 ሜትር ሩጫ የተሳተፈችው ሴት “ስፖርተኛም ሯጭም አይደለችም” ብለዋል።

“የሶማሊያ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ማሕበር” የሚባል ተቋምም እንደሌለ ሚኒስትሩ ጠቅሰው፣ የሶማሊያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሊቀ መንበር የሆኑት ካዲጆ ዳሂር እንዲታገዱ የሀገሪቱን የኦሎምፒክ ኮሚቴን ጠይቋል።

ናስሮ አቡካር አሊ የተባለችው እና በሩጫው የተሳተፈችው ሴት “በዘመድ አዝማድ የተመረጠች ነች” ሲሉ ሚኒስትሩ ከሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG