በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኢትዮጵያ ጦሯን ጁባላንድ ክልል  አስገብታለች” ስትል ሶማሊያ ከሰሰች 


"ኢትዮጵያ ዛሬ ዓርብ ወደ ደቡባዊ ጁባላንድ ክልል ጦር ልካለች" ስትል ሶማሊያ ከሰሰች፡፡

የሶማሊያ የማስታወቂያ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ "ኢትዮጵያ ጦሯን ደቡብ ጌዶ ክልል ወደሚገኘው ቡሎሃዎ አንቀሳቅሳ የነበረ ቢሆንም፣ በታጣቂ ኃይሎችና በአካባቢው ማኅበረሰብ ግስጋሴው ሊገታ ችሏል" ብሏል።

“የኢትዮጵያ መንግሥት በጌዶ ክልል በጎሣዎች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚፈጽመውን የሚኮነን ድርጊት በጽኑ እናወግዛለን” ብሏል ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፡፡

“ይህ የአዲስ አበባው መንግሥት በሶማሊያ አንድነትና ሉዐላዊነት ላይ የሚፈጽመው የጣልቃ ገብነት እንቅስቃሴ አካል ነው” ያለው መግለጫ “ሃገሪቱ በሰላም አብሮ መኖርን ብትመርጥም፣ የኢትዮጵያ ድርጊት ግን በቀጣናው አዲስ ግጭት የሚፈጥር ነው” ሲልም አክሏል።

ሶማሊያ “ነጻነቷንና ሉዐላዊነቷን ለመከላከል” ዝግጁ ነች ያለው መግለጫ፣ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ "ተፈፀመ" ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲያወግዝ ጠይቋል።

አዲስ አበባ በሶማሊያ መግለጫ ላይ አስተያየት እንዳልሰጠች የጠቆመው የኤ ኤፍ ፒ ዘገባ፣ የባለሥልጣናትን አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG