በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አልሸባብ የሶማልያን ምርጫ ለማሰናከል ዝቷል


የሶማልያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ መሀመድ (ፎርማጆ) ባላፈው ግንቦት ወር ከየማህበረሰቡ ለተወከሉ መራጮች ንግግር ሲያደርጉ
የሶማልያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ መሀመድ (ፎርማጆ) ባላፈው ግንቦት ወር ከየማህበረሰቡ ለተወከሉ መራጮች ንግግር ሲያደርጉ

የሶማልያ አሸባሪ ቡድን አልሸባብ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በሶማልያ በሚደረገው ምርጫ፣ ህግ አውጭ የምክር ቤት አባላትን ለመምረጥ ከየአካባቢው ማህበረሰብ በተሰየሙ ተወካዮች ላይ ጥቃት እንደሚሰነዝር አስጠንቅቋል፡፡

እስላማዊው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን በአፍሪካ ቀንድ ሶማልያ የሚካሄደው መጭውን ፕሬዚዳንታዊና የህዝብ ተወካዮች ምርጫ እንደሚያውክ አስጠንቅቋል፡፡

የቡድኑ መሪ መሀመድ አቡ ኡቤዳ ባላፈው ማክሰኞ እንደተናገረው የምርጫውን ሂደት የሚቃወም መሆኑን ገልጾ በመራጭነት የሚሳተፉ ተወካዮችንም እንደሚከተለው አስጠንቅቋል፡፡

“በመራጭነት የተወከሉ ተወካዮች ተስፋ በተደረገላቸው ገንዘብም ሆነ በሚስጥራዊ የድምጽ አሰጣጥ በመሳሰሉት መደለል የለባቸውም፡፡ እኤአ በ2017 በተደረገው ምርጫ የተሳተፉት ልኡካን የገጠማቸውን እጣ ማስታወስ ይገባቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ የተገደሉ ሲሆን አንዳንዶቹ አሁን ድረስ በፍርሃት ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡”

አልሸባብ የሶማልያን ምርጫ ለማሰናከል ዝቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:33 0:00

እኤአ በ2017 በተካሄደው ምርጫ በመራጭነት ከተወከሉት ውስጥ ለተገደሉት በርካታ ሰዎች አልሻባብ ኃላፊነቱን መውሰዱን አስታውቋል፡፡

የቡድኑ መሪ ኡቤዳ አሁንም ቢሆንም በዘንድሮው ምርጫ በመራጭነት እንዲሳተፉ የተወከሉ ሁሉ ውሳኔያቸውን እንዲመረምሩና የአልሸባብን ማስጠንቀቂያ የሚጥሱ ሰዎች ደህንነታቸው አደጋ ላይ መሆኑን እንዲገነዘቡ አስጠንቅቋል፡፡

ምርጫው የሚጀመረው በሚከተለው እሁድ ሲሆን ከየጎሳው ማህበረሰብ የተወከሉ 54 ተወካዮች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይመረጣሉ፡፡

የቀድሞ የሶማልያ ደህንነት ተቋም ምክትል ዳይሬክተር አብዲሳለም ጉሌድ በቅርቡ የወጣው ማስጠንቀቂያ በምርጫው ሂደት የሚሳተፉ ሰዎችን ለማስፈራራት የተቃደ ነው ይላሉ፡፡

“ቡድኑ መጭውን ታሪካዊ ምርጫ አስመልክቶ የሰጠው ማስጠንቀቂያ በቀላሉ ሊታይ የሚገባው ነገር ሳይሆን የተቀናጀ ምላሽ የሚሻ ነው፡፡ ምንም እንኳ ማስጠንቀቂያው በምርጫው ሂደት ላይ ተጽእኖ ሊኖረው ቢችልም በአፍሪካ ቀንድ የሚካሄደውን ዲሞክራሲያዊ ሂደት የማስቀረት ዓላማውን ግን የሚያሳካለት አይሆንም፡፡

የሶማልያ የጸጥታ አስካባሪ ኃይሎች ሶማልያ ውስጥ ካሉት የአፍሪካ ህብረት ኃይሎችና አሚሶም ጋር በመተባበር የምርጫውን ሂደትና ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ እየሰሩ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በሶማልያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የደህንነት ዋና አማካሪ የሆኑት አብዲ ደርሺ በቅርብ የተሰነዘረውን ዛቻና ማስፈራሪያ ለመመከት የማይፈነቀል ድንጋይ አይኖርም ያላሉ፡

“የታጣቂውን የአልሸባብ ቡድን አስመልከቶ ያለው የፌደራል መንግስቱ ፖሊሲ በጣም ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ተሸንፈው ከአገሪቱ ይወገዳሉ፡፡ በመላ አገሪቱ ምርጫው የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች በሙሉ ደህንነት የተጠበቀ ለማድረግ የወጣ የደህንነት እቅድ አለ፡፡”

በምርጫው ሂደት ላይ በነረበው አለመግባባት የሶማልያ ምርጫ ለአንድ ዓመት ያህል መዘግየቱ ይታወሳል፡፡ ህግ አውጭዎቹ የፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፎርማጆን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም ጥረት ቢያደርጉም በተቃዋሚዎችና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተነሳ ተቃውሞ ሙከራው ሊቀለበስ ችሏል፡፡

(የቪኦኤ ዘጋቢ መሀመድ ካዬከሞቃድሾ ከላከው ዘገባ የተወሰደ፡፡)

XS
SM
MD
LG