ዋሺንግተን ዲሲ —
የሶማልያ ምክር ቤት አባላት ቀጣዩን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ በሰጡት ድምጽ “ፋርማጆ” በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ የበዛ ድምፅ በማግኘት ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንትነት ሆነው ተመርጠዋል።
የሶማልያ ምክር ቤት ሁለት ዙር ምርጫ ከአካሄደ በኋላ ነው ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ ያሸነፉት። ተሿሚኚው መሪ ሐሰን ሼኽ ሞሐመድ ዛሬ መሸነፋቸውን ተቀብለዋል።
ፋርማጆ ከስድስትና አምስት አመታ በፊት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት አላቸው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ