በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ክፍለ ግዛት ሱል ውስጥ በተነሳ ግጭት ሥልሳ ሰዎች ተገደሉ

ሰሜናዊው የሶማሊያ ክፍለ ግዛት ሱል ውስጥ የተቀናቃኝ ነገዶች ታጣቂዎች ተጋጭተው ቢያንስ ሥልሳ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችና ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ።

ሰሜናዊው የሶማሊያ ክፍለ ግዛት ሱል ውስጥ የተቀናቃኝ ነገዶች ታጣቂዎች ተጋጭተው ቢያንስ ሥልሳ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችና ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ።

ዱሁልባሃንቴ በሚባለው ነገድ ውስጥ ሁለት የተለያዩ ቡድኖች ሚሊሽያዎች ትናንት ሰኞ ጠዋት ያነሱ ሲታኮሱ የቆዩት በመሬት ባለቤትነትና በቂም በቀል ምክንያት መሆኑን ነው የገለፁት።

ከሞቱት ሌላ ከዘጠና የሚበልጡ ሰዎች መቁሰላቸው ታውቋል። አንዳንዶቹ በተኩስ ልውውጡ መሃል የተጠመዱ ሲቪሎች ናቸው ተብሏል።

የሶማሊያ መንግሥት ሁለቱ ወገኖች ተኩስ አቁመው የሰላም ንግግር እንዲያካሂዱ ተማፅኗል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG