ከአንድ ሣምንት በፊት ሞቃዲሾ ከተማ በሚገኘው ትልቁ ባርካ ገበያ ከፈነዳውና ቢያስን ስምንት ሰዎችን ከገደለው ቦንብ ፍንዳታ በስተጀርባ ማን እንዳለ ለማወቅ የከተማዋ ባለሥልጣናት እየጣሩ ነው።
ፍንዳታው ተያይዘው በተሠሩ የኤሌክትሮኒክስ መሸጫ መደብሮች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን የንግድ ባለንብረቶች ተናግረዋል።
የሞቃዲሾ ባለሥልጣናት ፍንዳታው የደረሰው በመደብሮቹ ውስጥ በተቀበረ ፈንጂ መሆኑን ከመግለፅ ውጪ፣ ከፍንዳታዎቹ በስተጀርባ ስላለው ምክያንት ምንነት አልገለፁም።
ይሁን እንጂ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የመስጠት ፈቃድ ያልተሰጣቸው በመሆኑ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አንድ የደህንነት ሠራተኛ፤ የጥቃቶቹ ምክንያት በመደብሮቹ ውስጥ ከተተከሉ የደህንነት ካሜራዎች ጋር የተያያዘ መሆኑን ለአሜሪካ ድምጽ የሶማልኛው ቋንቋ አገልግሎት ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ዓመት የሶማልያ የደህንነት ተቋማት የንግድ ባለቤቶች የደህንነት ካሜራዎችን እንዲተክሉ አሳስበው ነበር።
አንዳንዶቹ የንግድ መደብሮች ባለቤቶች፣ የካሜራዎቹን መተከል ከሚቃወሙና የእስላማዊ ጽንፈኛ ቡድን አልሻባብ አባል መሆናቸውን ከገለፁ ያልታወቁ ሰዎች የማስጠንቀቂያ ጥሪ ደርሷቸው እንደነበር ተናግረዋል።
መድረክ / ፎረም