በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረትን ልዑክ የሚተካውን ኃይል ለመምራት ጠየቀች


አፍሪካ ህብረት፣ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
አፍሪካ ህብረት፣ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ልዑክ የተሰኘው ኃይል በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ላይ ሃገሪቱን ለቆ ሲወጣ የሚተካውንና ከሃገራት የሚውጣጣውን ኃይል መምራት እንደምትሻ ሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረትን ጠይቃለች፡፡

ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የቀረበውን ሃሳብ በመልካም እንደሚቀበል የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የፀጥታ ም/ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ከሃገራት የሚውጣጣው ኃይል ከሚቀጥለው የፈረንጆ አዲስ ዓመት ጀምሮ ለአንድ ዓመት በሃገሪቱ እንደሚቆይ ታውቋል።

በኃይሉ ውስጥ የየትኞቹ ሃገራት ወታደሮች እንደሚሳተፉ የሶማሊያ ባለሥልጣናት ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። የሶማሊያው ፕሬዝደንት ብሔራው የፀጥታ አማካሪ የሆኑት ሁሴን ሼክ አሊ ባለፈው የካቲት ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ መጠይቅ እንዳሉት፣ አዲሱ ኃይል “ሳሳ ያለ” እንደሚሆንና፣ በአገሪቱ የሚገኙ ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን፣ ኤምባሲዎችን እንዲሁም የዓለም አቀፍ ድርጅቶች የአቅርቦት ማዕከላትን የሚጠብቅ ብቻ እንደሚሆን አስታውቀው ነበር።

ኃይሉ ከአል ሻባብ ጋራ በሚደረገው ፍልሚያ እንደማይሳተፍና፣ ከሶማሊያ ኃይሎች ጋራ በቅርብ እንደሚሠራ፣ በሂደትም የሶማሊያ ኃይሎች ሥራውን እንደሚረከቡ ብሔራው የፀጥታ አማካሪው አስታውቀው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG