በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አልሸባብ ኬንያ ድንበር ላይ ጥቃት አደረሰ

የሶማልያው አሸባሪ ቡድን አልሸባብ፣ ከኬንያ ጋር በሚያገናኘው ድንበር ላይ በምትገኝ አንድ ቁልፍ ከተማ ላይ ዛሬ ሰኞ ጥቃት ማካሄዱን ነዋሪዎች ተናገሩ።

የሶማልያው አሸባሪ ቡድን አልሸባብ፣ ከኬንያ ጋር በሚያገናኘው ድንበር ላይ በምትገኝ አንድ ቁልፍ ከተማ ላይ ዛሬ ሰኞ ጥቃት ማካሄዱን ነዋሪዎች ተናገሩ።

ጥቃቱ የተጀመረው ነውጠኛው ቡድን ማለዳ ላይ ከተማዮቱን ከሁሉም አቅጣጫ ከወረረ በኋላ መሆኑም ታውቋል።

ሁለት የሂሊድ ሃዎ ነዋሪዎች እንዳስታወቁት፣ የአል ሻባብ ተዋጊዎች በመጀመሪያ ከከተማይቱ ሥድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን ወታደራዊ ጦር ሰፈር አጥቅተዋል።

ሁለተኛው ጥቃት የተፈፀመው፣ ከተማይቱ ውስጥ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያው ላይ ባነጣጠረ ወታደራዊ ውጊያ መሆኑን፣ አንድ የሂሊድ ሃዎ የቀድሞው አስተዳዳሪ ገልፀዋል።

በፖሊስ ጣቢያው ላይ አካባቢ ከባድ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱም ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG