በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ጸረ አል-ሻባብ የቲቪ ፕሮግራም ጀመረች


የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ ሞሃመድ ፕሮግራሙን በይፋ ካስጀመሩ
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ ሞሃመድ ፕሮግራሙን በይፋ ካስጀመሩ

የሶማሊያ መንግሥት በአል-ሻባብ ላይ የሚካሄደውን ዘመቻ በዋናነት የሚዘግብ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ዛሬ ረቡዕ ጀምሯል።

አዲሱ ቻነል ኤስኤንቲቪ በተባለው በሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቭዥን ሥር የሚተላለፍ ሲሆን ኤስኤንቲቪ ዳልጂር (ወታደሩ) በመባል ተሰይሟል።

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ ሞሃመድ ፕሮግራሙን በይፋ ካስጀመሩ በኋላ እንደተናገሩት፣ ቻንሉ በኻዋሪጆቹ ላይ የሚደረገው ጦርነት አንዱ አካል ነው ብለዋል። ኻዋሪጅ - ከእስልምና ያፈነገጠ ሰው እንደማለት ሲሆን መንግሥት አል-ሻባብን ለመግለጽ የጠቀምበታል።

“ዋናው አስፈላጊ ጉዳይ ትክክለኛ መረጃና ዜና፣ ትክክለኛውን ሃይማኖት፣ ትክክለኛውን ርዕዮተ-ዓለም እና ትክክለኛውን አርበኝነት እንዲሁም መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ ለሕዝቡ ማሳወቅ ነው” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ በሥነ-ሥር ዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር።

ፕሮግራሙ በተለይ በአል-ሻባብ ስለ እስልምና ሃይማኖት የተሰጠው ትርጉም ትክክለኛው ትርጉም አለመሆኑን ለህዝቡ አስረግጦ ያስተምራል ብልዋል ፕሬዚዳንቱ አክለው።

ይህ በአንዲህ እንዳለ ባለፉት ሦስት ወራት በተደረገ ዘመቻ የጸጥታ ኃይሎች 600 የአል-ሻባብ ተዋጊዎችን ሲገድሉ 1200 የሚሆኑትን ደግሞ ማቁሰላቸውን የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ ተናግረዋል።

የካቢኔያቸውን የመጀመሪያ መቶ ቀናት ሪፖርት ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ባሬ አክለውም 68 መንደሮችን ከአል-ሻባብ ማስለቀቃቸውን አስታውቀዋል።

አል-ሻባብ በበኩሉ አንዳንድ አካባቢዎችን መልሶ መቆጣጠሩንና በደርዘን የሚቆጠሩ የመንግስትና አጋር ወታደሮችን መግደሉን ይገልጻል።

በሁለቱም ወገን የሚባለውን በገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልተቻለም።

XS
SM
MD
LG