በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አልሸባብ ለዓመታዊ የመሳሪያ ግዢ 24 ሚሊየን ዶላር እንደሚያወጣ አንድ ሪፖርት ይፋ አድረገ


ፎቶ ፋይል፦ የአልሸባብ ተዋጊዎች፤ በሞቃዲሹ ሶማሊያ
ፎቶ ፋይል፦ የአልሸባብ ተዋጊዎች፤ በሞቃዲሹ ሶማሊያ

"አልሸባብ" የተሰኘው በሶማሊያ የሚንቀሳቀስ ታጣቂ ቡድን 24 ሚሊየን ዶላር ዓመታዊ በጀት ለመሳሪያ ግዢ እንዳዋለ አንድ ሪፖርት ይፋ አደረገ።

መቀመጫውን ሞጋዲሹ ላይ ባደረገው ሂራል የተሰኘ ተቋም ይፋ የተደረገው ሪፖርት ፣ ቡድኑ ከውጭ ሀገራት በተለይ ደግሞ ከየመን መሳሪያዎችን ለመግዛት እና ለመረከብ በቀጥታ ጥቁር ገበያን፣ የመሳሪያ ደላሎች እና ሻጮችን የመሳሳሉ የተለያዩ መንገዶችን እንደሚጠቀም አስታውቋል።

ሂራል ተቋም፣ የአልሻብብ ሩብ በጀት የሚፈሰው ቅድሚያ በሰጣቸው መሳሪያዎች ጥይቶች፣ ፈንጂዎች እና አውዳሚ ቁሶች ግዢ ላይ እንደሆነ ጠቁሟል።

“ከ100 ሚሊየን ዓመታዊ ግዢው ውስጥ፣ አልሸባብ ለመሳሪያዎች ግዥ የሚያወጣው ወጪ 24 ሚሊየን ዶላር፣ በወር 2 ሚሊየን ዶላር ያህል ነው” ብሏል ሪፖርቱ ።

ሳሚራ ጌይድ የተባሉት የሂራል ተቋም ኃላፊ አልሸባብ የተወሰኑ ጥይቶችን እና ፈንጂዎችን እንደሚያመርትና የተወሰነ በጀቱም ለዚሁ ዓለማ እንደሚያውል ጠቁመዋል።

አልሸባብ ለመሰል ተግባራት የሚያውለውን ገንዘብ ለማግኘት ውስብስብ የገንዘብ ማሰባሰብ ሥርዓትን እና ከሶማሊያ የንግድ ሰዎች ቀረጥ ማስከፈልን የመሰሉ ስልቶችን እንደሚጠቀም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የባለሙያዎች ቡድን ቀደም ባለው ጊዜ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG