በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አልሸባብ የክልል ኃላፊዎችን ዒላማ ያደረጉ የቦምብ ጥቃቶችን አደረሰ


ፎቶ ፋይል፦ የታጠቁ የአልሸባብ አባላት፣ ሞቃዲሾ፤ ሶማሊያ
ፎቶ ፋይል፦ የታጠቁ የአልሸባብ አባላት፣ ሞቃዲሾ፤ ሶማሊያ

ሶማሊያ ውስጥ በደቡብ ጌዶ ክልል ባርድኺር ከተማ ትናንት ማክሰኞ ጧት በደረሰው የአጥፎቶ ጠፊ የቦምብ ፍንዳታ በርካታ ጉዳቶች መድረሳቸው ተነገረ፡፡

ፍንዳታው የደረሰው፣ በከማዪቱ ማዕከላዊ ሥፍራ በሚገኘው የባለሥልጣኖች መኖሪያ ህንጻ፣ ፈንጅ ከተጠመደበት መኪና መሆኑን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቪኦኤ የሶማሊኛ ክፍል ተናግረዋል፡፡

በአደጋው በትንሹ ሁለት ወታደሮች ሳይሞቱ እንዳልቀሩና በርካታ ሰዎችም መቁሰላቸውን ነዋሪው ገልጸዋል፡፡

የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ለፍንዳታው ኃላፊነቱን የወሰደው ወዲያውኑ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የቦምቡን አደጋ ያደረሰው አጥፍቶ ጠፊ የጸረ አልሸባብ ዘመቻ ላይ ሲወያዩ የነበሩ የክልል ባለሥልጣናት ወደነበሩበት ህንጻ፣ ፈንጅ የተጠመደበት መኪናውን በቀጥታ ይዞ በመግባት የፈጸመው መሆኑን ቡድኑ በማኅበራዊ ሚዲያው ቴሌግራም ላይ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ካለፈው ነሀሴ ጀምሮ በማህበረሰብ ደረጃ የፌዴራል መንግሥት ኃይሎች ያንቀሳቀሱትን ዘመቻ ተከትሎ፣ አልሸባብ በማዕከላዊ ሶማሊያ የነበሩትን ጠንካራ ይዞታዎቹን ማጣቱ ተነግሯል፡፡

አልሸባብም በወሰዳቸው የበቀል እምርጃዎች፣ በጸረ አልሸባብ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ የሆኑትን ከተሞች፣ የጎሳ ሽማግሌዎችንና የአካባቢ ሚሊሻ አዛዦችን ዒላማ ያደረጉ ተከታታይ ጥቃቶችን አድርሷል፡፡

XS
SM
MD
LG