በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአል-ሻባብ ለ7 ሰዓታት የተፈጸመው እገታ አበቃ

በአል-ሻባብ ለሰባት ሰዓታት በአንድ የመኖሪያ ሕንጻ ላይ የተፈጸመውን እገታ እንዲያበቃ ማድረጋቸውን የሶማሊያ ጸጥታ ኃይሎች አስታውቀዋል፡፡
በአል-ሻባብ ለሰባት ሰዓታት በአንድ የመኖሪያ ሕንጻ ላይ የተፈጸመውን እገታ እንዲያበቃ ማድረጋቸውን የሶማሊያ ጸጥታ ኃይሎች አስታውቀዋል፡፡

በአል-ሻባብ ለሰባት ሰዓታት በአንድ የመኖሪያ ሕንጻ ላይ የተፈጸመውን እገታ እንዲያበቃ ማድረጋቸውን የሶማሊያ ጸጥታ ኃይሎች አስታውቀዋል፡፡

በምሥራቅ ሞቃዲሹ በሚገኝ የጦር ጉዳተኞች ማገገሚያ ላይ በተፈጸመው እገታ 10 ሰዎች በአል-ሻባብ ተዋጊዎች መገደላቸውንና 7 ሌሎች ደግም መቁሰላቸውን የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሟቾቹ በማዕከላዊ ሶማሊያ በአል-ሻባብ ላይ በተደረገው ዘመቻ የተጎዱ እንደነበር ታውቋል፡፡

ሟቾቹን “ሰማዕት” ብሎ የገለጸው የሚኒስቴሩ መግለጫ ግድያውን የፈጸሙት አራት የአል ሸባብ አባላት መገደላቸውን አስታውቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በማዕከላዊ ሸበሌ ክልል በተደረገ ዘመቻ 42 የአል-ሻባብ ተዋጊዎች መገደላቸውን የሶማሊያ መንግስት አስታውቋል፡፡

30 ሰዓታት በፈጀው ዘመቻ የመንግሥት ኃይሎች፣ የአካባቢው ተዋጊዎች እንዲሁም ዓለም አቀፍ አጋሮች መሳተፋቸውን የማስታወቂያ ሚኒስቴሩ መግለጫ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG