ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎችና የሶማልያ መንግሥት ባካሄዱት የተቀናጀ የአየር ጥቃት፣ አንድ አሸባሪ መገደሉን፣ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ ዛሬ ሰኞ አስታወቁ።
በዕዙ መግለጫ መሠረት፣ ጥቃቱ ዛሬ ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ላይ ነው በእስላማዊ ተዋጊ ኃይሎቹ ላይ የተካሄደው።
“የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል ጥቃቱ ቀጣይ መሆኑን ያመለከተው አፍሪካው ዕዝ፣ ይህም ከአሚሶም እና ከሶማልያ ብሔራዊ ደኅንነት ኃይሎች ጋር በመተባበር የሚካሄድና ሽብርተኞች ላይ የሚያነጣጥር መሆኑንም አመልክቷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ