በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ሀገሪቱን ለቆ መውጣቱን በ90 ቀን እንዲያዘገይ ሶማሊያ ጠየቀች


የሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ
የሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ

በግጭት የተናጠችው ሶማሊያ፣ ሀገሪቱን በመልቀቅ ላይ ያለው የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ሂደቱን በሶስት ወር እንዲያዘገይ ጠይቃለች ሲል የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተመልክቼዋለሁ ያለውን የመንግስት ሰነድ ጠቅሶ ዘግቧል።

ከአል ሻባብ ሚሊሺያ ጋር በመደረግ ላይ ባለው ፍልሚያ “በርካታ ከባድ ችግርች” እንደገጠመው ያስታወቀው የሶማሊያ መንግስት፣ በሃገሪቱ የጸጥታ አማካሪ በኩል ለተመድ በጽሁፍ ባቀረበው ጥያቄ፣ በዚህ ወር መጨረሻ ሊወጣ ያቀደው 3ሺሕ የሚቆጠር ሰምላም አስከባሪ ኃያል፣ ሂደቱን እንዲያዘገይ ጠይቋል።

ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች እና ሌሎች ምንጮች ጥያቄው መቅረቡን አረጋግጠዋል ሲል ኤኤፍፒ በዘገባው አመልክቷል።

በደቡብ እና ማዕከላዊ ሶማሊያ ላለፉት 16 ዓመታት የመንግስትን ይዞታና መሬትን ሲጠብቅ የነበረው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ልዑክ፣ ወይም ከሁለት ዓመታት ወዲህ በሚጠራበት “በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ልዑክ” ሀገሪቱን ለቆ መውጣት ጀምሮ ነበር።

በተመድ ውሳኔ መሠረት በመጪው የፈረንጆ ዓመት መጨረሻ የልዑኩ ኃይል የሀገሪቱን ጸጥታ የመጠበቅ ኃላፊነት ለሶማሊያ ሰራዊት አሳልፎ መስጠቱን ያጠናቅቃል ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG