በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካ ነክ ርዕሶች


አፍሪካ ነክ ርዕሶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:27 0:00

አፍሪካ ነክ ርዕሶች

በሶማሊያ ላይ የተጣለው የመሣሪያ ማዕቀብ ዓላማውና እና ምክንያቱ አሁን ካለው ሁኔታ ጋር አይጣጣምም በሚል፣ የአገሪቱ ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ የጸጥታው ም/ቤት ማዕቀቡ እንዲያነሳ ተማጽነዋል። አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት ግን፣ አገሪቱ የምትገዛቸው መሣሪያዎች አሸባሪዎች እጅ ስላለመግባታቸው ማስተማመኛ የለም።

ሕገ ወጥ የመሣሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር መንግሥታቸው በቂ የአሠራር ዘዴ በተግባር ላይ እንዳዋለ ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ ለጸጥታው ም/ቤት አስታውቀው መሣሪያን በባለቤትነት መያዝ፣ ማምረት፣ ማከማቸት እና አጠቃቀምን በተመለከተ መንግሥት ሕግ ማውጣቱን ተናግረዋል።

የሶማሊያው መሪ አያይዘውም፣ የአሁኗ ሶማሊያ፣ የጸጥታው ምክር ቤት ማዕቀቡን በተጣለበት ወቅት እ.አ.አ 1992 ዓም የነበረችው ሶማሊያ አይደለችም ብለዋል።

በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ልዑክ ኃላፊ የሆኑት ሞሃመድ ኤል አሚን ሶፍ የፕሬዝደንቱን ጥሪ አስተጋብተዋል። ሃላፊው አክለውም፣” አገሪቱ አል ሻባብን በመዋጋት ረገድ ያስመዘገበችውን ውጤት ጠብቆ ለማቆየት እና በቡድኑ ላይ የሚደረገው ጥቃት ቀጣይነት እንዲኖረው ዓለም አቀፍ የተቀናጀ ጥረት አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

ሶማሊያ በአል ሸባብ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ነች፡፡ “የጥቁር አንበሳ ዘመቻ” ብሎ የሰየመውን ሁለተኛ ዙር ዘመቻ በአል ሻባብ ላይ ለመጀመር መንግስት በዝግጅት ላይ ነው። በመጀመሪያው ዙር ዘመቻ የሶማሊያ ሠራዊት እና የጎሳ ሚሊሺያዎች ተሳትፈዋል። ባለፈው ጥር ከአገራቱ ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት፣ በሁለተኛው ዙር ዘመቻ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ጅቡቲ የሚመደቡ ወታደሮች ይሳተፋሉ።

የተለያዩ ተንታኞችን ምልከታ ያካተተውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG