ዋሺንግተን ዲሲ —
የሶማሊያ ባለሥልጣናት ፈንጂ የተጫኑ መኪናዎች ተከታትለው ከጦር ሰፈሩ ጋር በመላተም ፍንድታውን ካደረሱ በኋላ ከሁለት በኩል ተኩስ እንደከፈቱበት ነው የገለፁት።
ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደው አልሸባብ ቢያንስ ሃምሳ የመንግሥት ወታደሮች ገድያለሁ ብሉዋል። መንግሥት ስድስት ሰው ተገድሎብናል ነው ያለው ።
የታችኛው ሸበሌ ክፍለ ግዛት አገረ ገዢ ኢብራሂም አደን ናጃህ ለቪኦኤ የሶማሊኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል የመንግሥት ኃይሎች 23 የአልሸባብ ነውጠኛ ገድለዋል ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ