በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሌ ክልል የመስኖ ልማት ዕቅድ


የሶማሌ ክልል የመስኖ ልማት ዕቅድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:32 0:00

የሶማሌ ክልል መንግሥት 847ሺ ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት ማቀዱን አስታወቀ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሒም ኦስማን ክልሉ በከርሰ ምድርና ገጸ ምድር በውሃ ሃብት የበለጸገ መሆኑን ገልጸው ይሄንኑ ሃብትና ለእርሻ ምቹ የሆነውን መሬት በመጠቀም የክልሉ ምርታማነት ለመጨመር ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።

በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን አዲጋላ ወረዳ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሀመድ የመሩትና የፌዴራልና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል። ሚኒስትሯ በዞኑ የተጀመሩ የመስኖ ልማት ፕሮጄክቶች በአፋጣኝ ተጠናቀው ስራ እንዲጀምሩ የእርሳቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የሚጠበቅበትን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የሶማሌ ክልል በክልሉ የተከሰተውን አስከፊ ድርቅ ተከትሎ ለመስኖ ልማት ትኩረት መስጠት እንደሚጀመር አስታውቆ የነበር ሲሆን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ግን እቅዱን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር እክል ሊያጋጥመው ይችላል ሲሉ ሥጋታቸውን ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG